በምዕራብ ጉጂ ዞን ቡሌ ሆራ ከተማ 60 የጥይት ካዝና በጎመን ውስጥ ጠቅልሎ በህገወጥ መንገድ ሊያሳልፍ የማከረው ግለሰብ በቁጥጥር ሥር ዋለ

ዕረቡ ነሐሴ 11 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በኦሮሚያ ክልል፣ ምዕራብ ጉጂ ዞን ቡሌ ሆራ ከተማ መናኸሪያ ላይ 60 የጥይት ካዝና በጎመን ጠቅልሎ በህገወጥ መንገድ ለማሳለፍ የማከረው ግለሰብ በህብረተሰብ ጥቆማ በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የቡሌ ሆራ ፖሊስ አስታወቀ።

በትላንትናው ዕለት ከጠዋቱ 5 ሰዓት አካባቢ ከሲዳማ ክልል፤ ጩኮ አከባቢ የተነሳው ግለሰቡ መዳረሻውን ያቤሎ በማድረግ፤ በእስር ጎመን ውስጥ 60 የጥይት ካርታ በመደበቅ ለጥፋት አካላት ሊደርስ ሲል በቁጥጥር ሥር መዋሉን ፖሊስ ገልጿል።

ፖሊስ ግለሰቡ በቁጥጥር ሥር ውሎ ጉዳዩ እያጣራ እንደሚገኝ የገለጸ ሲሆን፤ ህቡረተሰቡ መሰል ድርጊቶችን የሚፈጽሙ የጥፋት ሀይሎችን ለጸጥታ አካለት አሳልፎ በመስጠት የሚያደርገውን ትብብር አጠናክሮ እንዲቀጥል ማሳሰቡን ከቡሌ ሆራ ኮሚኒኬሽን ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply