በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ ከሽንፋ ቀበሌ ወደ ገንዳ ውሃ ሲያቀና በነበረ የጭነት መኪና ላይ ተኩስ የከፈቱ ሽፍቶች አንድ የፖሊስ አባልን በመግደል ሾፌሩን ጨምሮ 4 ሰዎችን አግተው መው…

በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ ከሽንፋ ቀበሌ ወደ ገንዳ ውሃ ሲያቀና በነበረ የጭነት መኪና ላይ ተኩስ የከፈቱ ሽፍቶች አንድ የፖሊስ አባልን በመግደል ሾፌሩን ጨምሮ 4 ሰዎችን አግተው መው…

በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ ከሽንፋ ቀበሌ ወደ ገንዳ ውሃ ሲያቀና በነበረ የጭነት መኪና ላይ ተኩስ የከፈቱ ሽፍቶች አንድ የፖሊስ አባልን በመግደል ሾፌሩን ጨምሮ 4 ሰዎችን አግተው መውሰዳቸው ተሰማ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 16 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ ከሽንፋ ቀበሌ ወደ ገንዳ ውሃ ከተማ ዛሬ የካቲት 16 ቀን 2013 ዓ.ም ሲያቀና በነበረ ኤፍ አስ አር የጭነት መኪና ላይ ተኩስ የከፈቱ የቅማንት ተወላጅ የሆኑ ሽፍቶች አያናው አለሙ የተባለ የሽንፋ ቀበሌ የፖሊስ አባልን በመግደል ሾፌሩን ጨምሮ 4 ሰዎችን አግተው ስለመውሰዳቸው ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመልክቷል። ጥቃቱ የተፈፀመው ከጠዋቱ 2 ሰዓት ገደማ በመተማ ወረዳ ለምለም ተራራ በተባለ አካባቢ ነው ያሉት ነዋሪዎች ለምለም ተራራ ታጣቂዎች በንፁሃን ላይ ተደጋጋሚ ጥቃት የሚያደርሱበት መሆኑን አውስተዋል። በአካባቢው የመከላከያ ሰራዊት ካምፕ ቢኖርም ይህ የግድያና የዘረፋ ወንጀል ሲፈፀም ለመድረስ አልቻሉም ሲሉ ነዋሪዎች ወቅሰዋል። ዛሬ በተፈፀመው ነውረኛ የግድያና ዝርፊያ ወንጀል የተሰማሩ ሽፍቶች 4 ሰዎችን አግተው የወሰዱ ሲሆን 5ኛዋ ታጋች ሴት ለመጓዝ አልቻለችም በሚል ደብድበው ጥለዋት እንደሄዱና አሁን ላይ ወደ መተማ ሆስፒታል ለህክምና እርዳታ መወሰዷን ነው የመረጃ ምንጮች የገለፁት። በተደጋገሚ የእገታ፣ የግድያና የዝርፊያ ወንጀል ከተሰማሩት ሽፍቶች መካከል አንደኛው ከሟች ፖሊስ በተተኮሰ ጥይት መገደሉንና ፖሊሱም በሟች ግብረ አበሮች መገደሉን ከደረሰን መረጃ ለመረዳት ተችሏል። ድርጊቱ ከተፈፀመበት ጊዜ ጀምሮ የፀጥታ አካላት ስምሪት ላይ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል። ስለጉዳዩ ተጨማሪ መረጃ እንዲሰጡን በሚል የአማራ ሚዲያ ማዕከል በተደጋጋሚ የደወለላቸው የመተማ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ፈንታሁን ኪሮስ ፈቅደው ስልካቸውን ባለማንሳታቸው ለጊዜው ሀሳባቸውን ለማካተት አልቻለም። አሚማ የታገቱት እነማን እንደሆኑ ተጨማሪ መረጃ ይዞ የምንመለስ ይሆናል። ከአካባቢው ነዋሪ ጋር ያደረግነውን ቆይታ በአሚማ የዩቱብ አድራሻ የምናጋራ ይሆናል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply