በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ዮሃንስ የአብን የወጣቶች አደራጅ ጉዳይ ኃላፊ በጥይት ተገደለ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ   ሚያዝያ 14 ቀን 2013 ዓ.ም         አዲስ አበባ ሸዋ የምዕራ…

በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ዮሃንስ የአብን የወጣቶች አደራጅ ጉዳይ ኃላፊ በጥይት ተገደለ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሚያዝያ 14 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የምዕራ…

በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ዮሃንስ የአብን የወጣቶች አደራጅ ጉዳይ ኃላፊ በጥይት ተገደለ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሚያዝያ 14 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የምዕራብ ጎንደር ዞን የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የአብን እጩ ተወዳዳሪ አቶ አግባው ሰጠኝ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው እንዳጋሩት የዘንድሮው በግድያ የታጀበው ምርጫ መተማ መድረሱን ጠቅሰው አማኑኤል ጥሩነህ የተባለ የምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ የአብን ወጣቶች አደራጅ ጉዳይ ሀላፊ ትናንት ምሽት ሁለት ሰአት ላይ በጥይት ተመትቶ ህይወቱ አልፏል። አቶ አግባው መንግስት በአስቸኳይ ጉዳዩን እንዲያጣራ እንጠይቃለን! ለቤተሰቦቹ መጽናናትን እንመኛለን! የሚል መልዕክትም አስተላልፈዋል። የአማራ ሚደያ ማዕከል ጉዳዩን ለማጣራት የአካባቢው ነዋሪዎችንና የሚሊሻ ጽ/ቤት ባለሙያን አነጋግሯል። ግድያው የተፈፀመው በአንድ የከተማው ነዋሪ ትናንት ምሽት ሁለት ሰዓት ላይ መሆኑን የጠቀሱት ነዋሪዎችና የሚሊሻ ባለሙያ በሽጉጥ ግድያ ፈፅሟል የተባለ አንድ የግል ታጣቂም በቁጥጥር ስር መዋሉን አመልክተዋል። ለጊዜው ከዚህ ያለፈ ለፖለቲካ አላማ የተፈፀመ ግድያ ስለመሆኑ በቂ መረጃ ለማግኘት አልቻልንም፤ ተጨማሪ መረጃ እንዳገኘን እንመለሳለን።

Source: Link to the Post

Leave a Reply