በምዕራብ ጎንደር ዞን ቋራ ወረዳ በሚገኘው በአልጣሽ ብሔራዊ ፓርክ ውስጥ ሰደድ እሳት መከሰቱ ተሰማ! ታሕሳስ 6 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ባህርዳር ዝሆን፣ አንበሳ፣ ነብርና አቦ ሸማ…

በምዕራብ ጎንደር ዞን ቋራ ወረዳ በሚገኘው በአልጣሽ ብሔራዊ ፓርክ ውስጥ ሰደድ እሳት መከሰቱ ተሰማ! ታሕሳስ 6 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ባህርዳር ዝሆን፣ አንበሳ፣ ነብርና አቦ ሸማኔን ጨምሮ 32 ትላልቅ አጥቢ የዱር እንስሳትና ከ180 በላይ የአዕዋፋት ዝርያዎች ያሉበት የአልጣሽ ብሔራዊ ፓርክ የሰደድ እሳት ተከሰተ። በምዕራብ ጎንደር ዞን ቋራ ወረዳ በሚገኘው በአልጣሽ ብሔራዊ ፓርክ ውስጥ ሰደድ እሳት መከሰቱን የቋራ ወረዳ ኮሚኒኬሽን ቢሮ አስታውቋል ። የሰደድ እሳቱ በአልጣሽ ብሔራዊ ፓርክ በርሚል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከሰሞኑን መከሰቱ ተነግሯል ። ሰደድ እሳቱን ለመቆጣጠር እየተደረገ ስላለው ሁኔታ ማወቅ ባይቻልም በቀጣይ ለብሔራዊ ፓርኩ ስጋት መሆኑ ተገልጿል ። የአልጣሽ ብሔራዊ ፓርክ የህልውና ስጋት እንደገጠመው ከአሁን ቀደም መዘገቡ ይታወሳል ። በፓርኩ ብርቅዬ እንስሳት የሆነውን ጥቁር ባለጋማ አንበሳን ጨምሮ ሌሎች የቱሪስት መዳረሻ መሆን የሚችሉ የዱር እንስሳት ያሉት ብሔራዊ ፓርክ እንደሆነ ተሰይሟል፡፡ የአልጣሽ ብሔራዊ ፓርክ = = = = = አልጣሽ ብሔራዊ ፓርክ በአማራ ክልል በምዕራብ ጎንደር ዞን ቋራ ወረዳ ደቡብ ምዕራብ አቅጣጫ ይገኛል፡፡ 266 ሺህ 570 ሄክታር ስፋትና ከ500-900 ሜትር ከባሕር ወለል በላይ ከፍታ አለው፡፡ በቆዳ ስፋት በኢትዮጵያ 4ኛ በአማራ ክልል ደግሞ 1ኛ ደረጃን ይዟል፡፡ ከባሕር ዳር 460 ኪ.ሜ ከጐንደር 280 ከመተማ ዮሐንስ 163 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ በምዕራብ በኩል በሱዳን (#ዲንደር_ፓርክ)፣ በምስራቅና በሰሜን በኩል በወረዳው 7 ቀበሌዎች እንዲሁም በደቡብ በኩል በቤንሻንጉል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት (#አይማ_ወንዝ) ፓርኩን ያዋስኑታል፡፡ ፓርኩ ከ1970ዎቹ መጀመሪያ አንስቶ ‹‹ጥብቅ ደን›› የሚል ስያሜ ተሰጥቶት ጥበቃ ሲደረግለት ቆይቶ ከ1998ዓ.ም ጀምሮ ወደ ብሔራዊ ፓርክነት አድጓል፡፡ በፓርኩ ውስጥ ‹‹አላጥሽ›› የሚባል ወንዝ የሚገኝ በመሆኑ መጀመሪያ ላይ ፓርኩ ሲከለል የተሰጠው ስያሜ አላጥሽ የሚል ነበር፡፡ ‹‹አላጥሽ›› የሚለው ቃል ትርጉም በሚሰጥ ኢትዮጵያዊ በሆነ ቋንቋ መሰየም በማስፈለጉ በአዋጅ ቁጥር 333/2007 ‹‹አልጣሽ ብሔራዊ ፓርክ›› ተብሎ ተሰይሟል፡፡ በፓርኩ ውስጥ የሚገኘውን የብዝሐ-ሕይወት ሃብት በተመለከተ 32 ትላልቅ አጥቢ የዱር እንስሳት (ዝሆን፣ አንበሳ፣ ጎሽ፣ ነብር፣ አነር፣ አቦ ሸማኔ፣ ፌቆ፣ አጋዘን፣ ውድንቢ፣ ድኩላ፣ አምባራይሌ፣ ከርከሮ፣ ጥርኝ፣ ..ወዘተ)፤ 180 የአዕዋፍት ዝርያዎች (#የመስቀል_ወፍ፣ ጅግራ፣ ቆቅ፣ ዋኔ፣ ሰጎን፣ የግብጽ ዝይ፣ ድንቢጥ፣ ግንደ ቆርቁር፣ ጉጉት፣ መጎጥ…ወዘተ)፤ 8 ተሳቢ እንስሳት (ዘንዶ፣ አርጃኖ ….ወዘተ)፤ 16 የዓይጥ ዝርያዎች፤ 57 ትላልቅ የዛፍ ዝርያዎች (የእጣን ዛፍ፣ #እንኮይ፣ ዞቢ፣ ባምባ፣ ዘንባባ፣ ዋርካ፣ ሾላ፣ ችብሃ፣ ግማርዳ፣ ኩመር፣ ጋባ፣ ዶቅማ፣ ለንቋጣ፣ ግመሮ፣ ክርክራ፣ ሰርኪን፣ ሱማያ፣ ብርብራ፣ …ወዘተ)፤ 14 የተለያዩ የቁጥቋጦ ዝርያዎች፣ 10 ዓይነት የሳር ዝርያዎች እንዲሁም 16 ዓይነት የዓሳ ዝርያዎች (ቆረሶ፣ አንባዛ፣ በርሙጥ፣ ጥርሶ፣ ሃይላ፣ ጓንጃ፣ ለምለም ኩሬ፣ ሶርዝ፣ ተጋሎ፣ አይጦ፣ ሰፌዶ፣ ደረቅ ኩሬ፣ ጎሽ ምላስ፣ ዶለሴ፣ አደዝዝ እና አባቡቴ) እንደሚገኙ የአብክመ የአካባቢ የደንና የዱር እንስሳት ጥበቃና ልማት ባለስልጣን ያወጣው መረጃ ያመለክታል። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply