በምዕራብ ጎንደር ዞን በቋራ እና በመተማ አዋሳኝ አካባቢ የሽንፋ ወንዝ ለመስኖ ልማት እንዳይውል የሚቃወሙ ሽፍቶች ካገቷቸው 11 አማራዎች መካከል 10 የሚሆኑት ገንዘብ ከፍለው መለቀቃቸውን የ…

በምዕራብ ጎንደር ዞን በቋራ እና በመተማ አዋሳኝ አካባቢ የሽንፋ ወንዝ ለመስኖ ልማት እንዳይውል የሚቃወሙ ሽፍቶች ካገቷቸው 11 አማራዎች መካከል 10 የሚሆኑት ገንዘብ ከፍለው መለቀቃቸውን የ…

በምዕራብ ጎንደር ዞን በቋራ እና በመተማ አዋሳኝ አካባቢ የሽንፋ ወንዝ ለመስኖ ልማት እንዳይውል የሚቃወሙ ሽፍቶች ካገቷቸው 11 አማራዎች መካከል 10 የሚሆኑት ገንዘብ ከፍለው መለቀቃቸውን የቋራ ወረዳ ሰላምና ደህንነት ጽ/ቤት አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 1 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በምዕራብ ጎንደር ዞን በቋራ እና በመተማ ወረዳ አዋሳኝ አካባቢ የሽንፋ ወንዝ ለመስኖ ልማት እንዳይውል በሚቃወሙ የቅማንት ብሄረሰብ ተወላጅ በሆኑ ሽፍቶች ከደቡብ ጎንደር፣ ከጎጃምና ከተለያዩ አካባቢዎች መጥተው በመስኖ ስራ ተቀጥረው የነበሩ 11 የቀን ሰራተኞች ከአንድ ሳምንት በፊት ታግተው መውሰዳቸው ተገልጧል። ይህን ተከትሎም በመስኖ ልማት የተሰማሩ ባለሀብቶች ለእያንዳንዳቸው 30 ሽህ ብር በመክፈል 10 ሰራተኞችን እንዳስለቀቁ መረጃ ደርሶናል ሲሉ የቋራ ወረዳ አስተዳደር እና ፀጥታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ከፌ ተናግረዋል። ከመካከላቸው አንደኛው የቀን ሰራተኛ እስካሁን ድረስ እንዳልተለቀቀ ነው የደረሰን መረጃ ያመለከተው ብለዋል የፀጥታ ዘርፍ ኃላፊው። ከአሁን በፊት ሰው ሲገድሉና ሲዘርፉ ነበሩ የተባሉት ከቅማንት ብሄረሰብ የወጡ ሽፍቶች የአማራ ብቻ ሳይሆን የቅማንት ብሄረሰብም አሳልፎ ሰጥቶናል በማለት ጉዳት እያደረሱበት መሆኑን ነው አቶ ከፌ የገለፁት። አማራ እና ቅማንት በአንድ ላይ በሰላም መኖር የለበትም የሚል የጥፋት መንገድ ይዘው ይንቀሳቀሳሉ የተባሉት ሽፍቶች ለቋራ ወረዳ የፀጥታ አመራሮች ጭምር በመደወል ለማስፈራራት እየሞከሩ መሆኑ ተገልጧል። ይህን የጁንታው ትሕነግን ተልዕኮ እየፈፀሙ ያሉ አካላትም በስም ዝርዝር እንደሚታወቁና በመንግስት ጭምር የሚፈለጉ መሆኑን ነው አሚማ ያነጋገራቸው የፀጥታ ዘርፍ ኃላፊው ያረጋጡት።

Source: Link to the Post

Leave a Reply