You are currently viewing በምዕራብ ጎንደር ዞን ገንዳ ውሃ ከተማ 51 ሰዎችን በኤፍ ኤስ አር  የደረቅ ጭነት መኪና ጭኖ በህገ ወጥ መንገድ ወደ ሱዳን ሊያሻግር   ሲል የተያዘው ተከሳሽ የገንዘብ መቀጮ እና 11 (አስ…

በምዕራብ ጎንደር ዞን ገንዳ ውሃ ከተማ 51 ሰዎችን በኤፍ ኤስ አር የደረቅ ጭነት መኪና ጭኖ በህገ ወጥ መንገድ ወደ ሱዳን ሊያሻግር ሲል የተያዘው ተከሳሽ የገንዘብ መቀጮ እና 11 (አስ…

በምዕራብ ጎንደር ዞን ገንዳ ውሃ ከተማ 51 ሰዎችን በኤፍ ኤስ አር የደረቅ ጭነት መኪና ጭኖ በህገ ወጥ መንገድ ወደ ሱዳን ሊያሻግር ሲል የተያዘው ተከሳሽ የገንዘብ መቀጮ እና 11 (አስራ አንድ ) ዓመት የፅኑ እስራት ፍርድ ተፈረደበት። የአማራ ሚዲያ ማእከል ሐምሌ 16 2013 ዓ/ም አዲስአበባ ሸዋ ተከሳሹ አቶ ሰሎሞን ጥጋቡ ዕድሜ 32 ስራ የመኪና ረዳት አድራሻ ጎንደር ከተማ ቀበሌ 18 ሲሆን የመኪናው ሹፌር የሆነ ካልተያዘው ግብረ አበሩ አቶ ፈላው ተብሎ ከሚጠራው ግለሰብ ጋር በመሆን መተማ ወረዳ ገንዳ ውሃ ከተማ ቀበሌ ዐ2 ላይ ሐምሌ 02 ቀን 2013 ዓም በግምት ከረፋዱ 5:00 ሲሆን ከተለያየ የሀገሪቱ ክፍል አንስተው በህገ ወጥ መንገድ ወደ አውሮፖ ሀገር ለመሻገር የመጡትን 51 ሰዎች ጎንደር ከተማ ላይ ከደላሎች በመቀበል ወደ ሱዳን እናሻግራችኋለን በማለት ኮድ 3–ታርጋ ቁጥሩ 32469 በሆነ ኤፍ ኤስ አር የደረቅ ጭነት መኪና አሰቃቂ በሆነ መንገድ በኬንዳ ሸፍነው በመጫን ወደ ሱዳን ሲያጓጉዛቸው ገንዳ ውሃ ከተማ ላይ እጅ ከፈንጅ ተይዟል።የገንዳ ውሃ ከተማ ፖሊስ ፅ/ቤትም ተከሳሹንና ተዘዋዋሪዎችን ወደ ፖሊስ ጣቢያ በመውሰድ የወንጀል ምርመራውን በማጣራት የምርመራ መዝገቡን ለምዕ/ጎ/ዞ/ዐቃቤ ህግ መምሪያ በመላክ አስወስኗል። የዞን ዐቃቤ ህግም የወንጀል ምርመራ መዝገቡ እንደደረሰው መዝገቡን የመረመረው ሲሆን ተከሳሹ ሮጦ ካመለጠው ካልተያዘው ግብረ አበሩ ጋር በመሆን ያልተገባ ጥቅም ለራሱ ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ 51 ኢትዮጵያዊ ዜጎችን በህገ ወጥ መንገድ ወደ ሱዳር አገር ለማሻገር በኤፍ አስ አር የደረቅ ጭነት መኪና ጭኖ በሸራ /ኬንዳ ለአዳጋ በሚያጋልጥ ሁኔታ ሸፍኖ ሲያጓጉዝ የተያዘ በመሆኑ የህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ ቁጥር 1178 /2012 አንቀፅ 8(3) መሰረት በማድረግ በከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ በመመሥረት ተከራክሯል። የዞን ከፍ/ፍ/ቤትም የዐቃቤ ህግን ምስክር ካዳመጠ በሗላ ተከሳሹ ጥፋተኛ ከመባሉ በፊት የዐቃ ህግን ክስ በማስረጃ እንዲያስተባብል ብይን ቢሰጥም ተከሳሹ የመከላከያ ምስክር የለኝም በማለት ለችሎቱ አሳስቧል። ፍ/ቤቱም በተከሳሹ ላይ የጥፋተኝነት ፍርድ ከሰጠ በሗላ የዐቃቤ ህግንና የተከሳሹን የቅጣት አስተያየት በመሥማት ዛሬ በቀን 16/11/2013 ዓም በዋለው ችሎት ተከሳሹንም ሆነ መሠል የወንጀል ድርጊት የሚፈፅሙ ግለሰቦችን ያርማል ፣ ያስተምራል ያለውን የ5000 ( አምስት ሺ ብር) የገንዘብ መቀጮ እና የ 11 (አስራ አንድ ) አመት ፅኑ እስራት ቅጣት ወስኗል። ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር በዜጎች ላይ የሚፈፀም አስከፊ የወንጀል ድርጊት ሲሆን ዜጎችን ለከፋ የሰባዊ መብት ጥሰት ይዳርጋል።ወንጀሉ በአብዛኛው መነሻውን አዲስ አበባ አድርጎ ከጎንደር — ምዕራብ አርማጭሆ መስመር ፤ከጎንደር –ጭልጋ—መተማ —ሱዳን መስመር ፤ አልፎ አልፎ ከባህርዳር –ሻሁራ –ቋራ መሥመር አድርጎ ወደ ሱዳን አገር የመተላለፊያ መስመሮች ናቸው።የፀጥታ አካሉ የመተላለፊያ መስመሮችን በጥብቅ በማስጠበቅ እና ኬላዎች ላይ ተገቢውን ፍተሻ በማድረግ የወንጀል ደርጊቱን በመከላከል ዜጎች በአዘዋዋሪዎች እና ደላሎች አማካኝነት የሚደርስባቸውን የሠባዊ መብት ጥሰት መከላከል ይገባል በማለት መልዕክታችን እናስተላልፋለን። መረጃው የምዕራብ ጎንደር ዞን ዐቃቤ ህግ መምሪያ ነው::

Source: Link to the Post

Leave a Reply