በምዕራብ ጎጃም ዞን ሰሜን አቸፈር ወረዳ መስከረም 8/2015 ዓ.ም በረዶ ቀላቅሎ በጣለ ዝናብ ከ16 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ሰብል መውደሙ ተገለጸ:: (መስከረም 19/2015 ዓ.ም አሻ…

በምዕራብ ጎጃም ዞን ሰሜን አቸፈር ወረዳ መስከረም 8/2015 ዓ.ም በረዶ ቀላቅሎ በጣለ ዝናብ ከ16 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ሰብል መውደሙ ተገለጸ:: (መስከረም 19/2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ) ምዕራብ ጎጃም ዞን ሰሜን አቸፈር ወረዳ ሻምብላ አብና ቀበሌ ጨሊያ ጎጥ መስከረም 8/2015 ዓ.ም በረዶ ቀላቅሎ የጣለው ዝናብ በቆሎ በጤፍ፣ በዳጉሳ፣ በገብስ ፣አተር ፣ባቄላ ፣በርበሬ በተሸፈነው 2መቶ 37 ነጥብ 5 ሄክታር መሬት ሰብል ልማት ላይ ሙሉ በሙሉ ጉዳት አድርሷል፡፡ በዚህም፦ – 1መቶ 51 አርሶ አደሮች የጉዳቱ ሰለባ ሆነዋል፤ – ጉዳት የደረሰባቸው ሰብሎች በምርት ዘመኑ 15ሺህ 1 መቶ 2 ነጥብ 5 ኩንታል ይገኛል ተብሎ ይጠበቅ ነበር፤ – የጠፋው ሰብል በገንዘብ ሲገመት 16 ሚሊዮን 86 ሺህ 1መቶ 12 ብር ይሆናል፤ – የ46 የአርሶ አደሮች ቤቶች እና 1 የእምነት ተቋም ላይ ጉዳት ደርሶባቸዋል፤ ጉዳቱ ከፍተኛ የኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ተፅዕኖ ማሳደሩን የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ንጉስ አለነ ገልጸው አርሶ አደሮችን መልሶ ለማቋቋም ከሚመለከተው አካል ጋር ውይይት በማድረግ ግብዓቶች እና ሌሎችን የማቅረብ ስራ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡ ጉዳቱ የደረሰባቸው አርሶ አደሮች በበኩላቸው ለርሀብና ለበሽታ እንዳይጋለጡ የሚመለከተው አካል አስፈላጊውን እርዳታ እንዲያደርግላቸውም ጠይቀዋል። መረጃው ሰሜን አቸፈር ወረዳ ኮሚኒኬሽን ነው:: ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply