You are currently viewing በምዕራብ ጎጃም ዞን ሰከላ ወረዳ የግሽ አባይ ከተማ ነዋሪዎች በወሎ ጋሸና እና ሀሙሲት ግንባር ወራሪዎችን ሲፋለሙ የተሰው የ9 ጀግኖችን አስከሬን በክብር ሸኝተዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…

በምዕራብ ጎጃም ዞን ሰከላ ወረዳ የግሽ አባይ ከተማ ነዋሪዎች በወሎ ጋሸና እና ሀሙሲት ግንባር ወራሪዎችን ሲፋለሙ የተሰው የ9 ጀግኖችን አስከሬን በክብር ሸኝተዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…

በምዕራብ ጎጃም ዞን ሰከላ ወረዳ የግሽ አባይ ከተማ ነዋሪዎች በወሎ ጋሸና እና ሀሙሲት ግንባር ወራሪዎችን ሲፋለሙ የተሰው የ9 ጀግኖችን አስከሬን በክብር ሸኝተዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 21 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በምዕራብ ጎጃም ዞን የሰከላ ወረዳ የግሽ አባይ ከተማ ነዋሪዎች በወሎ ጋሸና እና ሀሙሲት ግንባር አሸባሪውንና ወራሪውን ትሕነግ ሲፋለሙ የተሰው 9 ጀግና አርበኞችን አስከሬን ታህሳስ 21 ቀን 2014 ዓ.ም በፉከራ እና በሽለላ ታጅበው በክብር ሸኝተዋል። ስለ አማራ ህዝብ ህልውና ብሎም ስለ ሀገር ሲሉ ከሃዲን እየጣሉ በክብር ከተሰውት በርካታ የሰከላ ወረዳ ጀግኖች መካከልም በግሽ አባይ ከተማ በከፍተኛ ድምቀት ዛሬ የአስከሬን ሽኝት የተደረገላቸውም:_ 1) ፶ አለቃ በቀለ ይግዛው፣ 2) በላይ አልማው፣ 3) አታላይ ተሾመ፣ 4) አታላይ ጋሹ፣ 5) ዋለ መኩሩያ፣ 6) ጥሩነህ አጥናፍ፣ 7) ደባስ አላምረው፣ 😎 ምናለ ይርዳው 9) ክብሪት ልየው ናቸው። ስለአማራ ብሎም ስለኢትዮጵያ ብለው ዘምተው ውድ ህይወታቸውን አሳልፈው የሰጡ ከአሁን ቀደም ወደ ገጠርማ አካባቢ አሸኛኘት የተደረገላቸው 3፤ ዛሬ በግሽ አባይ ሽኝት የተደረገላቸው 9፣ እንዲሁም ገና ሽኝት ለማድረግ ቀጠሮ የተያዘላቸው በርካታ ቁጥር ያላቸው ስለእኛ የተሰው ጀግኖች ስለመኖራቸው ከአሚማ ጋር ቆይታ ካደረገው ከአካባቢው ነዋሪ እና ታጋይ ከፋለ ገበየሁ ንግግር ለመረዳት ተችሏል። ከፋለ ገበየሁ ግሽ አባይ ላይ በተደረገው የጀግኖች የአስከሬን ሽኝት ስነ ስርዓት ላይም በተተኮሰ ጥይት የአንድ ሰው ህይወት መጥፋቱ አሳዛኝ ስለመሆኑ በመጥቀስ የጥንቃቄ መልዕክትም አስተላልፏል። ክብር በተለያዩ አውደ ውጊያዎች በመሰለፍ ስለአማራ ብሎም ስለ ሀገር ስትሉ ውድ ህይወታችሁን አሳልፋችሁ ለሰጣችሁ ጀግኖች ይሁን!

Source: Link to the Post

Leave a Reply