በሞዛምቢክ በደረሰ የጀልባ መስመጥ የ94 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተነገረ

በሰሜናዊ ሞዛምቢክ በባህር ዳርቻ ላይ በተከሰተ የጀልባ መስመጥ ህፃናትን ጨምሮ የ94 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ፤ 26 የሚሆኑት መጥፋታቸውን የሀገሪቱ የባህር ትራንስፖርት ተቋም ገልጿል።

አደጋው የደረሰው ወደ በናምፑላ ግዝት ከሉንጋ ወደ ሞዛምቢክ ደሴት 130 ተጓዦችን ጭኖ የነበረ ጀልባ በማዕበል መመታቱን ተከትሎ የመስመጥ አደጋ መድረሱ ተገልጿል።

በዚህም ምክንያት በትንሹ የ94 ሰዎች ህይወት ማለፉን እና ለ26 ሰዎች መጥፋት ምክንያት መሆኑ ተመላክቷል።

የመስመጥ አደጋ የደረሰበት መርክብ የተጨናነቀ አና ሰዎችን ለማጓጓዝ ፍቃድ እንዳልነበረው የተቋሙ አስተዳደር ሎረንኮ ማቻዶ ለመንግሥት ቴሌቪዥን ጣቢያ ገልጿል።

አደጋው የደረሰባቸው ተጓዦቹም የኩሌራ ወረርሽኝን ሸሽተው በመጓዝ ላይ እንደነበሩ ሲኤን ኤን ዘግቧል፡፡

እሌኒ ግዛቸው

ሚያዚያ 01 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply