በሞዛምፒክ የጣለው ንፋስ የቀላቀለ ከባድ ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ ከ7 ሺ በላይ ሰዎች ሲፈናቀሉ ከፍተኛ የሰብል ውድመት አድርሷል፡፡

ከባዱ ዝናብ ካስከተለው ጎርፍ ባሻገር በሰዓት 150 ኪሎ ሜትር የሚምዘገዘግ ንፋስ መቀላቀሉም ታውቋል፡፡ ጎርፉ ከሞዛምፒክ ሶፋላ ኮስታል ግዛት ባሻገር በጎረቤት ሀገራት ዚምባብዌ፣ ስዋዚላንድና ደቡብ አፍሪካም ተዛምቶ ጉዳት ማድረሱ ተጠቁሟ፡፡

የሞዛምፒክ ብሄራዊ የአደጋ ስጋት መቀነስ ኢንስቲቲዩት ይፋ ባደረገው መረጃ ጎርፉና አውሎ ንፋሱ 6 ሺ 859 ሰዎችን ከቀያቸው አፈናቅሏል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ 136 ሺ 755 ሄክታር ሰብል፣ ዘጠኝ ትምህርት ቤቶችን እና 11 ሆስፒታሎችን ማውደሙን ዘገባው ጠቁሟል፡፡አደጋው ሰዎችን ከመኖሪያ ቀያቸው ከማፈናቀል ባለፈ በሺ የሚቆጠሩ ቤቶችን ማውደሙን በመጥቀስ አልጄዚራ ዘገባውን ቋጭቷል፡፡

*******************************************************************************

ቀን 17/05/2013

አሐዱ ራዲዮ 94.3

The post በሞዛምፒክ የጣለው ንፋስ የቀላቀለ ከባድ ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ ከ7 ሺ በላይ ሰዎች ሲፈናቀሉ ከፍተኛ የሰብል ውድመት አድርሷል፡፡ appeared first on አሐዱ ቲቪ እና ራድዮ 94.3.

Source: Link to the Post

Leave a Reply