በሞጆ ከተማ 2 መቶ የሚሆኑ የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ገንዘብ ካልከፈላችሁ አታልፉም በሚል መቆማቸዉ ተሰማ፡፡

2 መቶ የሚሆኑ እነዚህ የአሸዋ ገልባጭ የሲኖትራክ አሽከርካሪዎች እንደ ገለፁት በየቦታዉ ያለአግባብና ባልተለመደ መልኩ እንድንቆሙና ገንዘብ እንድንከፋል ተደርገናል ነው ያሉት።

ከዚህ በፊት አንድ ገልባጭ መኪና ከቦታው ጭኖ ሲወጣ እዛው በደረሰኝ የሚከፍል ነበር ተብሏል፡፡

አሁን ግን በየቦታው የኮቴ እየተባለ በሚሊሻ አካላት ያለ ሰዓት እያስቆሙ በግድ ገንዘብ እንድንከፍል እያደረጉ ነው ብለዋል።

በዚህም አልከፍልም ያሉ አሽከርካሪዎች ላይ በመንግሥት የሚሊሺያ አባላት ድብደባ ፣ እስር፣ እንዲሁም የመኪናቸው ጎማ እየተመታና ለተለያዩ እንግልት እየተዳረግን ነው ብለዋል ።

አሺከርካሪዎቹ እንደገለፁት እንዲህ ያለው ተግባር በፊትም አልፎ አልፎ የነበረ ቢሆንም አሁን ግን በግልፅ እንዳንሰራ ወጥተን እንዳንገባ እንዳንቀሳቀስ ሆነናል ነው የሚሉት ።

በመጨረሻም የሚመለከተው አካል አስቸኳ መፍትሄ ይስጠን ሲሉም ጠይቀዋል።

በልዑል ወልዴ

መጋቢት 13 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply