በሞጆ ደብረ /ስ/ቅ/ልደታ ወበዓታ ለማርያም መቃኞ ቤተክርስቲያን ላይ የእሳት አደጋ መድረሱ ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 30 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ…

በሞጆ ደብረ /ስ/ቅ/ልደታ ወበዓታ ለማርያም መቃኞ ቤተክርስቲያን ላይ የእሳት አደጋ መድረሱ ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 30 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በሞጆ ደብረ /ስ/ቅ/ልደታ ወበዓታ ለማርያም መቃኞ ቤተክርስቲያን ላይ መንስኤው ባልታወቀ ምክንያት የእሳት አደጋ መድረሱ ተገልጿል። የደብሩ አስተዳዳሪ መ/ም/ቀሲስ ዘካሪያስ በለው የእሳት አደጋው በትክክልም የተከሰተ መሆኑን በመጠቆም የአደጋው መንስኤ በመጣራት ላይ መሆኑም ገልጸዋል። የደረሰውን የጉዳት መጠን በተመለከተ የመቃኞ ቤተክርስቲያኑ የቅኔ ማኅሌት ክፍል ከነ ሙሉ ንብረቱ የማህሌት መገልገያዎችን ጨምሮ የምዕመናን ወንበሮች ማውጣት ሳይቻል ሙሉ ለሙሉ መውደሙ ታውቋል። ቤተ ክርስቲያኑን መልሶ ለመስራትም የሞጆ ከተማ ምዕመናን ከፍተኛ ርብርብ እያደረጉ መሆኑን ጠቅሶ የዘገበው ተዋህዶ ሚዲያ ማዕከል (ተሚማ) ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply