በሞጣ ከተማ አስተዳደር እና በሁለት እጁ እነሴ የምርጫ ጣቢያ የሞጣ 3 ቀበሌዎች እስካሁን የመምረጥ እድላቸው አለመወሰኑ አግባብ አይደለም፤ በቀበሌ ደረጃ 1,500 የመምረጥ ኮታም የዜጎችን የ…

በሞጣ ከተማ አስተዳደር እና በሁለት እጁ እነሴ የምርጫ ጣቢያ የሞጣ 3 ቀበሌዎች እስካሁን የመምረጥ እድላቸው አለመወሰኑ አግባብ አይደለም፤ በቀበሌ ደረጃ 1,500 የመምረጥ ኮታም የዜጎችን የ…

በሞጣ ከተማ አስተዳደር እና በሁለት እጁ እነሴ የምርጫ ጣቢያ የሞጣ 3 ቀበሌዎች እስካሁን የመምረጥ እድላቸው አለመወሰኑ አግባብ አይደለም፤ በቀበሌ ደረጃ 1,500 የመምረጥ ኮታም የዜጎችን የመምረጥ መብት ገዳቢ ነው ሲል የሞጣ አብን ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ተቃወመ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 30 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በምስራቅ ጎጃም ዞን በሞጣ ከተማ አስተዳደር እና በሁለት እጁ እነሴ የምርጫ ጣቢያ የሞጣ ከተማ 3 ቀበሌዎች እስካሁን የመምረጥ እድላቸው አለመወሰኑ አግባብ አይደለም ያለው የሞጣ ከተማ አብን ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ነው። የማስተባበሪያ ጽ/ቤቱ ሊቀመንበር አቶ አበበ ተመስገን በሞጣ ከተማ በቀበሌ ደረጃ 1,500 የመምረጥ ኮታም የዜጎችን የመምረጥ መብት ገዳቢ ነው ሲሉ ተናግረዋል። የሞጣ ከተማ 6 ቀበሌዎች እንዳሏት የገለፁት አቶ አበበ የነዋሪዎቿ ቁጥር ከ50 ሽህ በላይ ቢሆንም የቆዬ መረጃን በመጠቀም በተሰራው እስካሁን 3 ቀበሌዎች ብቻ እንደሚመርጡ ነው የሚታወቀው ብለዋል። በሞጣ ከተማ 13 የምርጫ ጣቢያዎች ሲኖሩ በእያንዳንዱ 1,500 ሰዎች እንዲመርጡ በተቀመጠው ኮታ መሰረት 19,500 ሰዎች ብቻ ይመርጣሉ ያሉት አቶ አበበ ከ50 ሽህ ህዝብ ከ30 ሽህ በላይ የመምረጥ እድል አያገኝም፤ ይህ ደግሞ የዜጎችን መሰረታዊ የመምረጥ መብትን የሚገድብና ለብልሹ አሰራር ጭምር የሚዳርግ ነው ብለዋል። ለሞጣ እና ለሁለት እጁ እነሴ ወረዳ ለምርጫ አስተባባሪ ጉዳዩን ብናቀርብም እስካሁን ተገቢ ምላሽ አላገኘንም ብለዋል_በሞጣ የአብን ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሊቀመንበር አቶ አበበ ተመስገን። የቀረበውን ቅሬታ መሰረት አድርገን የሞጣ እና የሁለት እጁ እነሴ ወረዳ የምርጫ ጉዳዮች አስተባባሪ ቤቴልሄም አሳዬን አነጋግረናል። አስተባባሪዋ እንዳሉት የሞጣ የ3ቱ ቀበሌዎች የመምረጥ ጉዳይን በተመለከተ ለቦርዱ ቅሬታ አቅርበን ምላሽ እየጠበቅን እንገኛል፤ ምላሹ በቅርብ ቀን ሲደርሰን እናሳውቃለን ብለዋል። የኮታው ቁጥር ትክክል መሆኑን የገለፁት አስተባባሪዋ በዚህ ጉዳይ ላይ የደረሰን ቅሬታ የለም ሲደርሰን ግን ለሚመለከተው የበላይ አካል የምናቀርበው ይሆናል የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply