
ትውልድ እና እድገቱ ሰሜን ኢትዮጵያ ጎንደር ከተማ ነው። ኦሮምኛ ሲናገር ለሰማው ግን ዕድገቱ በኦሮሞ ማኅብረሰብ ውስጥ ሊመስለው ይችላል። የ30 ዓመቱ ዶ/ር ሃብታሙ ገበያው ኦሮምኛ ቋንቋ አንድ ብሎ መማር የጀመረው ግን ከሦስት ዓመታት በፊት ነበር። አሁን ላይ ቋንቋውን አቀላጥፎ ከመናገሩ ባሻገር ቋንቋውን ለመማር የሚያግዝ የኦሮምኛ ቋንቋ ሰዋሰው መጽሐፍ ማዘጋጀት ችሏል።
Source: Link to the Post