
ከሁለት ዓመት በላይ በዘለቀ ደም አፋሳሽ የእርስ በርስ ጦርነት በተደቆሰችው ትግራይ ክልል የሰፈነው ረሃብ እና የምግብ እጦት የነዋሪዎች የየቀን እውነታ ሆኗል። የሰላም ስምምነቱ ውጊያውን ቢያቆመውም የጦርነቱ ዳፋ ክልሉን እንዳጠለሸው ነው። የመንግሥታቱ ድርጅት በነሐሴ ወር ባወጣው ሪፖርት መሠረት ከአምስት ዓመት በታች በሆኑ ህጻናት ከሦስቱ አንዱ በተመጣጠነ ምግብ እጥረት እንደሚሰቃይ ይፋ አድርጓል።
Source: Link to the Post