በረባ ባልረባው መገዳደል፤ በማንነት ምክንያት የሚደርስ የዜጎች ሞት ይብቃ

“ቢገድሉት ቢገድሉት የማያልቀው” የተባለለት ሰፊው ህዝብ እየሞተ መኖር ሰልችቶታል።

በመላ ሀገሪቱ ስርዓት አልበኝነት ነግሷል። ሞት አንደ ዘበት ደግሞ ደጋግሞ እየመጣ ዙሪያችንን ያምሰዋል፡፡ህግ ማስከበር የአንድ ሉአላዊት ሀገር መንግስት የመጀመሪያ ስራው ቢሆንም ይህ ተዘንግቷል።

ስርዓት አልበኞች ከህግ እና ስርአት በታች እስካልሆኑ ድረስ ማናችንም ከጥቃት ሰለባነት አንተርፍም!! ህግ እና ስርአት የማይከበርበት አገር በፍጹም አንደ አገር አይቆጠርም እና አገር ለማስቀጠል ሁሉም የየድርሻውን ይወጣ የአሐዱ ሬዲዮ ሳምንታዊ አቋም አሀዱ አንቀጽ።

አዘጋጅ እና አቅራቢ፡ ሊዲያ አበበ

ቀን 19/04/2013

Source: Link to the Post

Leave a Reply