You are currently viewing በረዶ ቀላቅሎ የጣለው ዝናብ ለንፁህ መጠጥ ውሀ አቅርቦት የሚሰጡ ጉድጓዶች እና የውሃ ሞተር ቤቶች ላይ ጉዳት አደረሰ፡፡  አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ    ነሃሴ 14 ቀን 2014 ዓ.ም…

በረዶ ቀላቅሎ የጣለው ዝናብ ለንፁህ መጠጥ ውሀ አቅርቦት የሚሰጡ ጉድጓዶች እና የውሃ ሞተር ቤቶች ላይ ጉዳት አደረሰ፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ነሃሴ 14 ቀን 2014 ዓ.ም…

በረዶ ቀላቅሎ የጣለው ዝናብ ለንፁህ መጠጥ ውሀ አቅርቦት የሚሰጡ ጉድጓዶች እና የውሃ ሞተር ቤቶች ላይ ጉዳት አደረሰ፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ነሃሴ 14 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በደሴ ከተማ አስተዳደር የመጠጥና ውሀና ፍሳሽ አገልግሎት የገራዶ ቁጥር 1፣ ቁጥር 2፣ ቁጥር 3 እና የገብረኤል ሞተር ቤቶች ላይ በከፍተኛ ሁኔታ በጎርፍ አደጋ ደርሶበታል። የደሴ ከተማ አስተዳደር መጠጥ ውሀና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ለከተማው ማህበረሰብ የንፁህ መጠጥ ውሀ ለማድረስ ጥረት እያደረገ ቢሆንም በክረምቱ ከፍተኛ የዝናብ መጠን ምክንያት የገራዶ ቁጥር 1፣ ቁጥር 2፣ ቁጥር 3 እና የገብረኤል ሞተር ቤቶች ላይ የገራዶ እና የቦርከና ወንዝ አቅጣጫውን ቀይሮ ወደ ውሀ ጉድጓዱ በመግባቱ የንፁህ መጠጥ ውሀ አቅርቦቱ በከፍተኛ ሁኔታ ችግር ገጥሞታል። የገራዶና የቦርከና ወንዝ አሁንም አቅጣጫውን በመሳት ተጨማሪ ጉዳት እንዳያሰሰከትል፣ የችግሩን አሳሳቢነት በመረዳት በቀጣይ ደረጃውን የጠበቀ የጎርፍ መቀልበሻ ስትራክቸር ለመስራት መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ የሁሉንም ተቋማት ተሳትፎ እንደሚጠይቅ ስለመገለጹ የደሴ ከተማ አስተዳደር ኮሚዩኒኬሽን ዘገባ አመልክቷል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply