
በዝናብ እጦት በድረቅ ውስጥ የከረሙት አካባቢዎች በርካታ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ከፍተኛ መጠን ያለው የበልግ ዝናብን እያገኙ ነው። አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ ክልሎች ውስጥ በሚጥለው ከባድ ዝናብ ምክንያት በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል። ባለሙያዎች እንደሚሉት እየጣለ ያለው የዝናብ መጠን ከዚህ በፊት በበልግ ወቅት ከሚዘንበው ከፍ ያለ ነው። ታዲያ በረዶ እስከ መጣል የደረሰው ይህ የበልግ ዝናብ በአሁኑ ወቅት ለምን በረታ?
Source: Link to the Post