በረጅም የሀገር ግንባታ ወቅት ካለፉት መንግስታት እስካሁኑ መንግስት ድረስ ለስልጣን ማራዘሚያነት የሚፈጥሯቸው ትርክቶች በዜጐች የጋራ እሴቶች፣ መብቶች ላይ ያተኮሩ ባለመሆኑ ኢትዮጵያ ለተራዘመ ግጭት ውስጥ እንድትገባ ዳርጓታል አሉ አቶ ታዬ ደንደዓ፡፡

የሰላም ሚንስቴር ዴዔታ አቶ ታዬ ደንደዓ የሀገረ መንግስት ግንባታችን ረጅም ዘመናት የወሰደ አሁንም መጠናቀቅ ያልቻለ መሆኑንን አንስተዋል።

ሀገር የሚገነባው በአንድ እጅ አይደለም ያሉት አቶ ታዬ ለምንወደው የሀገር መሪ ወይም የፖለቲካ ፓርቲ የምንሰራው ሳይሆን ለዘላቂ ሀገር ነው ብለዋል።

ሀገረ ግንባታ ስንል እያንዳንዱ ዜጋ ውስጥ ኢትዮጵያዊ ማንነት መቀረጽ በመሆኑ ለስራዎቻችን ጥንቃቄ ያሻዋል ብለዋል።

ይህንን ስራ ለመንግስት ለፓርቲ አሊያም ለትውልድ የምንተወው አይደለም ያሉት አቶ ታዬ መገናኛ ብዙሀን እጥፋቱችን መቅናት ማረም እንደሚገባቸው ተናግረዋል።

የማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን አንቂዎችም ሆኑ ሌሎቹ የሚዲያ አካላት ያላቸውን ሀይል አውቀው ለሀገሪቱ ዘላቂ ሰላም የድርሻቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።
ዛሬ በአዳማ ከተማ የሀገረ መንግስት ምስረታ በሚል ርዕሰ ለሚዲያ አካላት የሰላም ሚንስትር ከቅን ልቦች በጎ አድራጎት ጋር በመተበበር የምክክር መድረክ እያካሄደ ነው።

በያይኔ አበባ ሻምበል
ህዳር 26 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply