በሩሲያ ስፖንሰር ለሚደረጉ ተገንጣዮች እውቅና እንድሰጥ የሚጠይቅ ማንኛውንም ስምምነት አንቀበልም አለች ዩክሬንዩክሬን በሩሲያ ስፖንሰር ለሚደረጉ ተገንጣዮች እውቅና እንድሰጥ የሚጠይቅ ማንኛውን…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/MUN1_5NIs58YLWifmnqE65uAv7Z0GY1c6GL2vnDnrSwQ5OPSGWNXhu51lMPcBCdovAiK1vQRkHsvwli_hdPNspS47r56SPQgTBaLHNFz0emqRrZ4dd9eIbGTVfTxK-oCF3dfu2T8976XSe8MTMC8z4D8pKWyUm4dRg638e9DI8CiPByFpU-z3fh-dP_7UgjV8NNUQJsJ8JdWCOEWpvxLa7QTBxiccGwIh4Y2V9I_TwHjPZYTzDtlYNiGGwvrGRjK2XsZO6deHT_2PSnVYFTmrvYjogP0Lw67_p9358KSTQ5oR1Hh4LEfz7WfqPKWb0H0Q1Q8ZnzgM1WONkiruGIaZw.jpg

በሩሲያ ስፖንሰር ለሚደረጉ ተገንጣዮች እውቅና እንድሰጥ የሚጠይቅ ማንኛውንም ስምምነት አንቀበልም አለች ዩክሬን

ዩክሬን በሩሲያ ስፖንሰር ለሚደረጉ ተገንጣዮች እውቅና እንድሰጥ የሚጠይቅ ማንኛውንም ስምምነት አንቀበልም ብትልም ሩሲያ እንድትደራደራት እየተማፀነች ነው፡፡

ፕሬዝዳንቱ ትናንት ከ ሲ ኤን ኤን ጋር በነበራቸው ቆይታ በቀጥታ ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ለመወያየት ዝግጁ እንደሆኑ የገለፁ ሲሆን ጦርነቱን ለማስቆም ድርድር ብቸኛው መንገድ ነው ብዬ አምናለሁ ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የመደራደር ዕድሉን ለማስፋት የትኛውንም መንገድ የትኛውንም ዕድል መጠቀም እንዳለብን አምናለሁ የሚሉት ዜሌኒስኪ በሩሲያ ስፖንሰር ለሚደረጉ ተገንጣዮች እውቅና እንድሰጥ የሚጠይቅ ማንኛውንም ስምምነት ግን አልቀበልም ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዜሌኒስኪ የሩሲያን ወረራ በድርድር ማስቆም አልተቻለም ማለት ግን የሶስተኛው የአለም ጦርነት መጀመር ማለት ነው ብለዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ ሀገሬ የኔቶ አባል ሀገር ብትሆን ኖሮ ጦርነቱ ቀድሞ ነገር ባልተጀመረ ነበር ብለዋል፡፡

የኔቶ አባላት እኛን እንደ አጋር ለማየት ዝግጁ ከሆኑ መደረግ ያለበትን በፍጥነት ማድረግ አለባቸው፤ ምክንያቱም ሰዎች በየቀኑ እየሞቱ ነው ሲሉ ጥሪያቸውን ማስተላለፋቸውን ሲ ኤን ኤን ዘግቧል፡፡

ሔኖክ አሥራት
መጋቢት 12 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply