በሩሲያ ከደረሰው ዘግናኝ ግድያ በኃላ  ከጥቃቱ ጋር በተያያዘ  11 ሰዎች እንደታሰሩ የደህንነት ባለስልጣናት ተናግረዋል፡ የሩስያ የኤፍ.ኤስ.ቢ የፀጥታ አገልግሎት ለፑቲን እንደተናገረው አርብ…

በሩሲያ ከደረሰው ዘግናኝ ግድያ በኃላ  ከጥቃቱ ጋር በተያያዘ  11 ሰዎች እንደታሰሩ የደህንነት ባለስልጣናት ተናግረዋል፡

የሩስያ የኤፍ.ኤስ.ቢ የፀጥታ አገልግሎት ለፑቲን እንደተናገረው አርብ በሞስኮ አቅራቢያ በደረሰው አሰቃቂ ጥቃት 11 ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል ።ከነዚህ መካከል አራቱ በቀጥታ  የተሳተፉ  ሰዎችን መሆናቸውም  ገልጿል።

ተጨማሪ ተባባሪዎችን የመለየት ስራ እየተሰራ ነውም ሲል ኢንተርፋክስ የክሬምሊን ጠቅሶ ዘግቧል።

ሌሎች ተጠርጣሪዎችም በአቅራቢያው ወደሚገኝ ጫካ ሸሽተው ክትትል እየተደረገባቸው መሆኑንም አክለዋል።

ታጣቂዎቹ በሞስኮ አቅራቢያ በሚገኘው ታዋቂው የክሮከስ አዳራሽ ላይ ተኩስ ከፍተው ቢያንስ 93 ሰዎች ሲገድሉ፣ 187 ሰዎች መቁሰላቸውን የሩሲያ የደኅንነት አገልግሎት አስታውቋል ።

ከሟቹቹ መካከል ስምንቱ ህፃናትን ናቸው።ስድስት ሰዎች በፅኑ ተጎድተዋል ሲል አልጀዚራ ዘግቧል ።

ለጥቃቱ ታጣቂው የእስላማዊ መንግሥት (አይኤስ) ቡድን ኃላፊነቱን መውሰዱን በበይነ መረብ የወጣ አንድ ያልተረጋገጠ መግለጫ አመልክቷል።

የአሜሪካ ባለሥልጣናት በበኩላቸው አይኤስ ሩሲያን ለማጥቃት እንደሚፈልግ የሚያሳይ መረጃ ማግኘታቸውን ለቢቢሲ የአሜሪካ አጋር ሲቢኤስ ተናግረዋል።

ከሁለት ሳምንታት በፊት በሩሲያ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ዜጎቹ በርካታ ሰዎች በሚሰባሰቡባቸው ሕዝባዊ ስፍራዎች እንዳይሄዱ ማስጠንቀቂያ አስተላልፎ ነበር።
በዚህም ማስጠንቀቂያው ላይ “ጽንፈኞች በሞስኮ ሕዝብ በሚሰባሰቡባቸው ስፍራዎችን የጥቃት ዒላማ ለማድረግ ዕቅድ አላቸው” የሚል ሪፖርትን እየተከታተልኩ ነው ብሎ ነበር።

ኤምባሲው አርብ ምሽት ባወጣውም መግለጫ ጥቃቱ ወደደረሰበት ስፍራ ዜጎቹ ዝር እንዳይሉም ምክሩን አስተላልፏል።

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጥቃቱን አስመልክቶ ለሕዝባቸው መግለጫ ባይሰጡም፣ ምክትላቸው በጥቃቱ የቆሰሉ በፍጥነት እንዲያገግሙ ምኞታቸውን አስተላልፈዋል።

መጋቢት 14 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcas

Source: Link to the Post

Leave a Reply