በሩሲያ ጦርቱን በመቃወም ዋና ከተማዋን ሞስኮን ጨምሮ በ51 ከተሞች የተቃውሞ ሰልፍ እየተደረገ ነው፡፡

እስካሁን ከ1,000 በላይ ተቃዋሚዎች መታሰራቸው ተነግሯል፡፡

ዋና ከተማ ሞስኮን ጨምሮ በ51 ከተሞች ተቃዋሚዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አናዶሉ የዜና ወኪል ዘግቧል፡፡

በሩሲያ ከ1,000 የሚበልጡ ተቃዋሚዎች ሀገሪቱ በዩክሬን የምታደርገውን ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት በመቃወም በተደረጉ ሰልፎች ላይ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አንድ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት አስታውቋል።

እንደ ኦቪዲ-ኢንፎ ዘገባ ከሆነ ተቃዋሚዎቹ የተያዙት በ51የሩስያ ከተሞች እንዲሁም ከዋና ከተማዋ ሞስኮ እና ሁለተኛዋ ትልቋ ሴንት ፒተርስበርግ ከተማ ነው።

በሞስኮ ወደ 700 የሚጠጉ ሰዎች እና በሴንት ፒተርስበርግ ወደ 400 የሚጠጉ ሰዎች መታሰራቸውን OVD-Info ተናግሯል።

እንደ አናዶሉ ዘገባ እስካሁን በግጭቱ 57 የዩክሬን ወታደሮች እና ንጹሀን ህይወታቸው ማለፉን የሀገሪቱ ጤና ሚኒስትር ሲያሳውቅ 169 ያህሉ ደግሞ መጎዳታቸውን ተናግሯል፡፡

ያይኔአበባ ሻምበል
የካቲት 18 ቀን 2014 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply