በሩስያ ለሦስት ቀናት የሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ትላንት ተጀምሯል።ትላንት የተጀመረው ድምጽ አሰጣጥ ሂደት እስከ እስከ ነገ እሁድ ድረስ በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ይቀጥላል። ምርጫው ሩ…

በሩስያ ለሦስት ቀናት የሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ትላንት ተጀምሯል።

ትላንት የተጀመረው ድምጽ አሰጣጥ ሂደት እስከ እስከ ነገ እሁድ ድረስ በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ይቀጥላል።

ምርጫው ሩስያ ከዩክሬን በገነጠለቻቸው ግዛቶችም ጭምር እየተካሄደ ነው ተብሏል። በሩስያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ መራጮች በበይነ መረብም ድምጻቸውን እየሰጡ ነው።

በነፃ መገናኛ ብዙሀንና በታዋቂ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ላይ ወከባ በሚካሄድባት በሩስያ የ71 ዓመቱ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ለአምስተኛ የስልጣን ዘመን የሚወዳደሩበት የአሁኑ ምርጫ ያን ያህል አጓጊ አለመሆኑ ተነግሯል።

የፑቲን ተቀናቃኞች እስር ቤት ናቸው ወይም ከሀገር ተሰደዋል። ከሁሉም በላይ ዋነኛ ተቀናቃኛቸው አሌክሲ ናቫንሊ ባለፈው ወር በተያዙበት እስር ቤት ሕይወታቸው አልፏል። በአሁኑ ምርጫ የሚወዳደሩት ሦስት የተቃዋሚ ፓርቲዎች ተፎካካሪዎችም ብዙም የማይታወቁ ፖለቲከኞች ናቸው።

በዚህ የተነሳም ምርጫው የፑቲንን የስልጣን ዘመን ያራዝማል ተብሎ የሚጠበቅ ነው።ታዛቢዎች ከወዲሁ እንደሚናገሩት ምርጫው ነፃና ትክክለኛ ይሆናል ብለው አይጠብቁም።

የአውሮጳ ኅብረት አባል ሀገራት መሪዎች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሻርል ሚሼል ትላንት በኤክስ ገጻቸው  በተጀመረው ምርጫ በከፍተኛ ድምጽ ያሸነፉትን ቭላድሚር ፑቲንን እንኳን ደስ ያለዎት ለማለት እፈልጋለሁ ተቃዋሚ የለም፣ነጻነት የለም፣ ምርጫም የለም ሲሉ ተሳልቀዋል። 
 

መጋቢት 07 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook  https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Source: Link to the Post

Leave a Reply