በሩስያ ምግብ ቤቶች እና ሱቆች እየተዘጉ ነው፡፡በሩስያ የኮቪድ19 እንደ ገና ማገርሸቱን ተከትሎ ሱቆች እና ምግብ ቤቶች እየተዘጉ ይገኛሉ፡፡በሞስኮ የሚገኙ በርካታ ምግብ ቤቶች እና ሱቆች እን…

https://cdn4.telesco.pe/file/Wnrso-ECrggrbVjr1xNaNvXpHAXSfSVZ-QbLT7vJV_WINfqxx4aUV5YqGFhA9BrPlTmjekY46bCERaVnPOB_Xkw4oxlNG6mZDbahfCtWJEPOkc9VFzooKMyGs4EbdyJW9UnBrk6zzw3TjxFv6IwdQXAYAI5NnhBQw7U40cRK9c6eaBrZKSwgZOUxhlhWaHrdh76to5AExXIswDdvK0zP5RVfQzkUhnwh9tTYot2aPvI0ApU5hDT6XXJ2zoj9-OL5SH5etJQez1Tg0Wlau4of9GLSrkZmXijJEM-lzreOhA4OFyWMK3-v4iUkAy9NF-vrYeGE9ZCyfLVBPxSkKj2NGw.jpg

በሩስያ ምግብ ቤቶች እና ሱቆች እየተዘጉ ነው፡፡

በሩስያ የኮቪድ19 እንደ ገና ማገርሸቱን ተከትሎ ሱቆች እና ምግብ ቤቶች እየተዘጉ ይገኛሉ፡፡

በሞስኮ የሚገኙ በርካታ ምግብ ቤቶች እና ሱቆች እንዲዘጉ መንግስት ያስታወቀ ሲሆን አላስፈላጊ የሆኑ ምርቶች እንዳይሸጡ አስጠንቅቋል፡፡

ሀገሪታ በትላንትናው እለት ከፍተኛ የተጠቂዎች ቁጥር እና የማቾች ቁጥር ማስመዝገቧ ተከትሎ ነው ውሳኔው ያስተላለፈችው፡፡

በትላንትናው እለት በሀገሪቱ ከ40 ሺህ በላይ ዜጎች በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሲሆን ከ1ሺህ በላይ ዜጎች ሕይወታቸው ማለፉን ተሰምቷል፡፡

ከአውሮፓ ሀገራት ሩስያ ከፍተኛ የማቾች እና የተጠቂዎች ቁጥር ያስመዘገበች ሀገር ስትሆን አሁንም የቫይረሱ ስርጭት አይሎ ነው የሚገኝው፡፡

ይህ በመሆኑም ለሚቀጥሉት 11 ቀናት ምግብ ቤቶች ሱቆች እና ሌሎችም አገልግሎት መስጫ ቦታዎች ዝግ ሆነው እንዲቆዩ ውሳኔ አስተላልፋለች፡፡

እስካሁን ድረስ በሀገሪቱ 8.4 ሚሊየን ዜጎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን 235 ሺህ የሚጠጉ ዜጎች ደግሞ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው አልፋል ሲል የሀገሪቱ የዜና ወኪል የሆነው አር ቲቪ አስታውቋል፡፡

ሔኖክ ወ/ገብርኤል
ጥቅምት 19 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply