በሩብ አመቱ በቦንድ ግዢ ሰባት ነጥብ አምስት ሚሊየን ብር መሰብሰቡን የሲዳማ ክልል አስታወቀ፡፡

የሲዳማ ብሄራዊ ክልል የህዳሴ ግድብ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት በተያዘዉ በጀት አመት የተለያዩ ህዝባዊ ንቅናቄዎችን በማድረግ በርካታ ድጋፎች መሰብሰቡን አስታዉቋል፡፡

ክልሉ በአዲስ የተደራጀ በመሆኑ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤትን አቋቁሞና ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤቱ የሚያስፈለግዉን የሰዉ ሐይል በማደራጅት በክልሉ ከሚገኙ ወረዳዎች ጋር በማቀናጀት በርካታ ስራዎች ሲሰሩ መቆየታቸዉ ተግልጿል፡፡በተሰራው የንቅናቄ ተግባርም በአንድ ቀን 10- ሚሊየን ብር ከመጀመሪያዉ ዉሐ ሙሌት በኃላ ለመሰብሰብ ታቅዶ 6 ሚሊየን ብር መሰብሰቡን የጽህፈት ቤቱ ሃላፊ አቶ ክፍሌ ሐሜስ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

ከዚህ በፊት ቦንድ ግዢ የተፈጸመባቸዉ 1.5 ሚሊየን ብር ወደ ባንክ ገቢ እንዲሆን መደረጉንም አቶ ክፍሌ አክለዋል፡፡በተጨማሪም ቦንድ ያልተሰራላቸዉን የቦንድ ግዢዎች እንዲሰራላቸዉ መደረጉንም ጠቁመዋል፡፡ በሩብ አመቱም 7.5 ሚሊየን ብር ለህዳሴዉ ግድብ በተለያዩ ክንዋኔዎች መሰብሰቡን ሐላፊዉ ገልጸዋል፡፡

ቀን 12/05/2013

አሐዱ ራዲዮ 94.3

The post በሩብ አመቱ በቦንድ ግዢ ሰባት ነጥብ አምስት ሚሊየን ብር መሰብሰቡን የሲዳማ ክልል አስታወቀ፡፡ appeared first on አሐዱ ቲቪ እና ራድዮ 94.3.

Source: Link to the Post

Leave a Reply