በሩዋንዳ ከሙዝ የተዘጋጀ ነው የተባለውን ቢራ የጠጡ 11 ሰዎች ሞቱ::በሩዋንዳ ቡጌሰራ በተባለች ግዛት፤ የገና በዓል ከተከበረበት እለት ጀምሮ ሙዝን እንደ ግብዓት በመጠቀም የተዘጋጀውን ቢራ…

በሩዋንዳ ከሙዝ የተዘጋጀ ነው የተባለውን ቢራ የጠጡ 11 ሰዎች ሞቱ::

በሩዋንዳ ቡጌሰራ በተባለች ግዛት፤ የገና በዓል ከተከበረበት እለት ጀምሮ ሙዝን እንደ ግብዓት በመጠቀም የተዘጋጀውን ቢራ ከጠጡ ሰዎች መካካል 11 የሚሆኑት ለህልፈተ ሕይወት መዳረጋቸውን የሀገሪቱ የምርምራ ቢሮ አስታውቋል፡፡

ሌሎች 4 የሚሆኑት ሰዎች ሆስፒታል መግባታቸውን የገለጸው ቢሮው፤ በተደረገው ምርመራ መሰረት በቢራው ውስጥ ኢታኖል የተሰኘው ንጥረ ነገር በከፍተኛ መጠን መገኘቱን አመላክቷል፡፡

የሩዋንዳ የምግብና መድሃኒቶች ቁጥጥር ባለስልጣን በበኩሉ፣ ሰዎችን ለሞት ያበቃቸው ምክንያት ከዚሁ ንጥረ ነገር መብዛት ጋር ሊያያዝ እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡

ይህን ከሙዝ የተዘጋጀ ነው የተባለውን ቢራ ያዘጋጁ 5 ሰዎች፤ በህገ ወጥ መንገድ እንደሆነ ያረጋገጠው የምርመራ ቢሮው፤ በቁጥር ስር እንዲውሉም ተደርጓል ብሏል፡፡

ከነዚህ ሰዎች ሞት በኋላም ሰዎች ከሙዝ ጭማቂ የተዘጋጀ ነው የተባላውን ቢራ እንዳይጠቀሙ ሲባልም ሀገር አቀፍ ዘመቻ መጀመሩን ቢቢሲ አፍሪካ ዘግቧል፡፡

በጅብሪል መሃመድ
ታህሳስ 27 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply