በራያ ህዝብ የምክክር መድረክ የተገኙ ተሳታፊዎች የምርጫ ክልላቸው በሰሜን ወሎ ተደርጎ የሚበጃቸውን ለመምረጥ እንደሚፈልጉ አስታወቁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ   ታህሳስ 25 ቀን 2013 ዓ…

በራያ ህዝብ የምክክር መድረክ የተገኙ ተሳታፊዎች የምርጫ ክልላቸው በሰሜን ወሎ ተደርጎ የሚበጃቸውን ለመምረጥ እንደሚፈልጉ አስታወቁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 25 ቀን 2013 ዓ…

በራያ ህዝብ የምክክር መድረክ የተገኙ ተሳታፊዎች የምርጫ ክልላቸው በሰሜን ወሎ ተደርጎ የሚበጃቸውን ለመምረጥ እንደሚፈልጉ አስታወቁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 25 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ከትናንት ጀምሮ ዛሬ ታህሳስ 25 ቀን 2013 ዓ.ም በተደረገው የራያ ህዝብ የምክክር መድረክ የተገኙ በሽዎች የሚቆጠሩ ተሳታፊዎች ራያ ወሎ ነው፤ ወሎም አማራ ነው የሚል አቋማቸውን አራምደዋል፤ በደማቅ ጭብጨባም አረጋግጠዋል፤ ሀሳቡን ደግፈዋል። በታሪካዊ መድረኩ የተገኙ ተሳታፊ የሀገር ሽማግሌዎች የራያ ህዝብ በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ የምርጫ ጣቢያ ተዘጋጅቶለት የሚበጀውን ለመምረጥ እንደሚፈልግና ለዚህም እንደሚታገል አስታውቀዋል። ከአባቶችና ከወጣቶች በትናንትናው እለት የተዋቀረው ኮሚቴ አመራሮች የማንነት፣የእርስትና የቀጣዩን ምርጫ ጉዳዩን በተመለከተ ምን መመስል እንዳለበት አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። በተለይም በቀጣዩ ምርጫ ሲረግጣቸው በቆየውና በከፍተኛ መስዋዕትነት ነጻ በወጡበት የትግራይ ክልል ይሁኑ የሚለውን በፍፁም እንደማይቀበሉት ጠቅሰው፤ መንግስትም ሆነ የምርጫ ቦርድ እንዲያውቀው በጥብቅ አሳስበዋል። የምክክር መድረኩ በወጣቶችም፣በሀገር ሽማግሌዎችም ሆነ በሁሉም የህ/ሰብ ክፍሎች ዘንድ የሚቀጥል መሆኑን ገልፀዋል። በመድረኩ ጹሁፍ ያቀረቡት አቶ በአካል ንጉሴ የቀጣይ ምርጫ በትግራይ ክልል ሳይሆን በአማራ ክልል በሰሜን ወሎ መሆን እንዳለበት ተፈራርመው ለምርጫ ቦርድ እንደሚያስገቡ ነው መልዕክት ያስተላለፉት። በራያ ህዝብ የምክክር መድረክ የተገኙት በሸዋ የደራ አማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ሰብሳቢ መ/ር ሀይለ ሚካኤል አርዓያ በቅድሚያ በመስዋዕትነት ነጻ በመውጣታችሁ፤ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል። መ/ር ሀይለ ሚካኤል ሲቀጥሉ የሸዋ ደራ፣የመተከል እና ጥያቄዎችም በጋራ ትግል መመለሳቸው አይቀርም ብለዋል። በእጃችሁ ያለውን ነጻነት ለመውሰድ የሚጣድፉ በውስጣቸው ያሉ ነጣቂዎችን በመምከርና በመዘከር አስተካክሉ ያሉት መ/ር ሀይለ ሚካኤል በመጨረሻ እንደራጅ የሚል መልዕክትን አስተላልፈዋል። የውይይት መድረኩን ያስተባበሩትና ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የመጡት ዶ/ር ሲሳይ መንግስቴ በሸዋ የደራ የአማራ እና የመተከል አማራ ህዝብ ነጻ ይሆን ዘንድ ከጎናቸው የማይለዩ መሆናቸውን አረጋግጠዋል። ዶ/ር ሲሳይ መንግስቴ በመጨረሻም በራያ ውስጥ ደመወዝ እየተከፈላቸው ነገር ግን የራያ አማራን ህዝብ ለመከፋፈል የሚሰሩ አካላት ሀይ ሊባሉ እንደሚገባቸውና ለዚህም ከመንግስት ጎን ሆነውም እንደሚሰሩ ገልፀዋል። አማራ ነን ብሎ በሚያምነው የአማራ ህዝብ ከአማራው ተነጥሎ ሌላ ክልል ይመስርት፣ ልዩ ዞን ይሁን ወይም ብሄረሰብ የሚሉ አካላትን እንቅስቃሴ መቼም ቢሆን የማያወጣ ማደናገሪያና ተቀባይነት የሌለው ነው ብለውታል። የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለአካባቢው ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ ለማድረግም የድርሻቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል። ዝርዝሩን የምንመለስበት ይሆናል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply