በራያ ቆቦ ሰላማዊ ሰልፍ አድርሃችኋል የተባሉ ወጣቶችና የከተማ አስተዳደር አካላት ለእስር መዳረጋቸው ተሰማ። /// አሻራ ሚዲያ ጥቅምት 19/2013 ዓም ባህ…

በራያ ቆቦ ሰላማዊ ሰልፍ አድርሃችኋል የተባሉ ወጣቶችና የከተማ አስተዳደር አካላት ለእስር መዳረጋቸው ተሰማ። /// አሻራ ሚዲያ ጥቅምት 19/2013 ዓም ባህር ዳር /// … የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ አብን በአማራ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን ተደጋጋሚ ዘርንና ብሄርን መሰረት ያደረገ ጥቃት ለማውገዝ በሚል የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ በራያ ቆቦ መደረጉ እና የቆቦ ማህበረሰብ ለተገደሉት እና ለተገፉት የአማራ ማህበረሰብ አባላት ከፍተኛ ድምጽ ማሰማቱ የሚታወስ ነው፡፡ ይሁንና ሰልፉ በሰላማዊ መንገድ ከተጠናቀቀ በኋላ የሰልፉ አስተባባሪ ናቸው የተባሉ እና በሰልፉ ተሳትፋችኋል የተባሉ ወጣቶች ወደ እስር ቤት እየተወሰዱ እንደሆነ ምንጫችን ከራያ ቆቦ ለአሻራ ሚዲያ ገልጸውልናል፡፡ ለእስር ከተዳረጉት ወጣቶች ወይም የራያ ጢነኛ አባላት በተጨማሪ የቆቦ ከተማ አስተዳደር የስራ ሀላፊዎችም እንደሚገኙበት ምንጫችን አረጋግጠውልናል፡፡ እንደ ምንጫችን ገለጻ በሰላማዊ ሰልፉ ላይ በግፍ የተገደሉትን ፤የተፈናቀሉትን እና የተሳደዱትን አማራዎች ሁኔታ ከመቃዎም ባለፈ አንድ ፖለቲካዊን ሌሎች የክልሉንም ሆነ የፌደራሉን መንግስት የሚያንቊስሱ መፈክሮችም ሆነ ድምጾች አለመደመጣቸውን ገልጸውልናል፡፡ ዘጋቢ፦ማርሸት ፀሐው

Source: Link to the Post

Leave a Reply