በራያ ቆቦ ወረዳ የወርቄ አካባቢ ነዋሪዎች መንግስት በመሰረተ ልማት ረገድ ትኩረት እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 22 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበ…

በራያ ቆቦ ወረዳ የወርቄ አካባቢ ነዋሪዎች መንግስት በመሰረተ ልማት ረገድ ትኩረት እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 22 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በሰሜን ወሎ ዞን ራያ ቆቦ ወረዳ የወርቄ ቀበሌ አሸባሪውን ትሕነግ ክፉኛ ድባቅ የመቱ እና ቅስሙን በመስበር ከፍተኛ ዋጋ ያስከፈሉ አይንበረከኬ ጀግኖች ያሉበት አካባቢ ነው። አሚማ ከሰሞኑ ወደ ወርቄ አቅንቶ የአማራ ማህበራት ህብረት በጀርመን ለሰማዕታት ቤተሰቦች ያደረገው ድጋፍ መድረሱን በስፍራው ተገኝቶ አረጋግጧል። የወርቄ እና አካባቢውን ወግ እና ባህል፣ባህላዊ የግብይት ስርዓትና ሁለንተናዊ መገለጫዎችንና የኑሮ ሁኔታውን ተመልክቷል። በተለይ ከመሰረተ ልማት ጋር በተያያዘ ብዙ መንግስታዊ ትኩረት እንዳልተሰጠው ነዋሪዎች ተናግረዋል። ውሃ፣ መብራት፣ መንገድ፣ ቴሌ ኮምዩኒኬሽንና ሌሎች ችግሮችም እንዲፈቱላቸው ጠይቀዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply