#በራያ አላማጣ ዋጃ አሁን የለው ሁኔታ። አሻራ ሚዲያ ጥቅምት 27/2013 ዓ.ም ባህርዳር በወሎ ራያ አላማጣ እና ዋጃ አሁን ያለው የፀጥታ ሁኔታ ከ2-3 ኪ.ሜትር እር…

#በራያ አላማጣ ዋጃ አሁን የለው ሁኔታ። አሻራ ሚዲያ ጥቅምት 27/2013 ዓ.ም ባህርዳር በወሎ ራያ አላማጣ እና ዋጃ አሁን ያለው የፀጥታ ሁኔታ ከ2-3 ኪ.ሜትር እርቀት ላይ የህውሓት ልዩሀይል እና የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት ተፋጠው እንደሚገኙ ከቦታው ያናገርናቸው የአሻራ ሚዲያ ምንጮች ነግረውናል። በማህበረሰቡ፣በራያ ጢነኛ እና በመከላከያ ሰራዊቱ መካከል ጥሩ የሚባል መናበብ እንዳለ የገለፁልን የመረጃ ምንጫችን መከላከያ ሰራዊታችን የሚያስፈልገውን የምግብ እና የመጠጥ አቅርቦት የራያ ህዝብ እና የራያ ጢነኞች እያቀረቡ እንደሆነም ገልፀውልናል። በህውሓት በኩል መቀሌ ላይ በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ ምንም አይነት መረጃ ባይኖረንም እኛ የራያ አማሮች ለረጅም ጊዜ የሰላምን መንገድ መርጠን ችግሩ ይፈታል ብለን ብንጠብቅም ህውሓት ጦርነትን መርጧል ብለዋል። መከላከያ ሰራዊታችን ከህዝቡ በፊት እኔ ልውደቅ የሚል በራስ መተማመን የተገነባ ሰራዊት መሆኑን አሳይቶናል።በህዝቡ በኩልም ከኮምቦልቻ ጀምሮ ደም የመለገስ ፕሮግራም ላይ ነው። የህውሓት ሰዎች ህብረተሰቡን ቤት ለቤት በመዞር አማራ መጣልህ ሊያጠፋህ ነው።መሬትህን ሊቀማህ ነው እያሉ እየቀሰቀሱ እንደሆነ ሰምተናል ።የትግራይ ህዝብም መሳሪያውን እንያዘው እንጂ የምንሰራውን እናውቃለን እያለ እንደሆነ ሰምተናል ሲሉ የመረጃ ምንጫችን ገልፀውልናል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply