በራያ የተለያዩ አካባቢዎች በኩል በአሸባሪው ትሕነግ እየተፈጸሙ ያሉ ዘርፈ ብዙ በደሎች እንደሚያሳስቡት የምስራቅ አማራ ፋኖ ገለጸ፤ በመንግስት በኩል ጦርነቱ እንዳለቀ ተደርጎ መነገሩ አግባብ…

በራያ የተለያዩ አካባቢዎች በኩል በአሸባሪው ትሕነግ እየተፈጸሙ ያሉ ዘርፈ ብዙ በደሎች እንደሚያሳስቡት የምስራቅ አማራ ፋኖ ገለጸ፤ በመንግስት በኩል ጦርነቱ እንዳለቀ ተደርጎ መነገሩ አግባብ ባለመሆኑ አማራ እንዳይዘናጋ መክሯል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 21 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የምስራቅ አማራ ፋኖ አመራሮችና አባላት ከአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) በቆቦ ከተማ በሰጡት ቃለ መጠይቅ እንደገለጹት አሸባሪው ትሕነግ በራያ የተለያዩ አካባቢዎች ተደጋጋሚ ግፍ እና በደል እየፈጸመ ነው። ቡድኑ ትንኮሳ፣ ግድያ፣ዝርፊያ እና ማፈናቀሉን አጠናክሮ እንደቀጠለበት መሆኑን የጠቀሱት የምስራቅ አማራ ፋኖ አመራሮች መንግስት ተኩስ አቁሜያለሁ ማለቱን ተከትሎ የአማራ አፅመ እርስቶችና የትግል መሰረቶች የሆኑት ዋጃ፣ጥሙጋ፣ራያ አላማጣ፣ኮረም፣ባላ፣ጨርጨር፣ ሂጅራ፣ ኩፍቱ እና ሌሎች ቀበሌዎች ጭምር በአሸባሪው ትሕነግ ወረራ ስር መሆናቸውን አመልክተዋል። ከእነዚህ አካባቢዎች የአማራ ህዝብ ላይ በተደጋጋሚ የሞት፣ የመታፈን፣የመዘረፍ፣ የመሳደድ እና የመፈናቀል ዜና መስማት የተለመደ መሆኑም ተገልጧል። ለዚህ ሁሉ መፍትሄውም ጦርነት ቆሟል፤ ሰላም ነው ከሚል አጉል መዘናጋት ወጥቶ በአንድነት፣ በተደራጀ እና በተናበበ መልኩ መታገል፤ ፋኖን አጠናክሮ መደገፍ መሆኑ ተመላክቷል። በምስራቅ አማራ ፋኖ በኩል በጎንደር ፋኖ ወደ አንድ ለመምጣት የተሄደበትን ርቀት አበረታች መሆኑን በመቀበል በወሎ ብሎም አጠቃላይ በአማራ ፋኖ ወደ አንድ መጥቶ የአማራ ህዝብ ሰላም እና ደህንነት እንዲሰፍን፣ጥያቄዎቹ እንዲመለሱ የሚታገል መሆኑን አስታውቋል። በአፅመ እርስቶቹ ጉዳይ ባለቤቱ የአማራ ህዝብም ሆነ ፋኖ የማያውቀው አንዳች የድብብቆሽ ድርድር እንደማይኖር እና ካለም ተቀባይነት እንደማይኖረውም አሚማ ከምስራቅ አማራ ፋኖዎች ካደረገው ቆይታ ለመረዳት ችሏል። የአማራ ህዝብ መንግስት የጸጥታ አካሉን ባለህበት ጽና ማለቱን ተከትሎ በጠለምት፣በዋግኽምራ እና በራያ ሰፊ አጽመ እርስቶቹ እንደተወረሩና ንጹሃን ወገኖቹም በአማራዊ ማንነታቸው ብቻ ለፈርጀ ብዙ በደሎች የተዳረጉበት መሆኑ ግልጽ ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply