በራያ ግንባር ተደጋጋሚ ሽንፈትን እየተከናነበ የሚገኘው ከሃዲው ሕወሓት ያሰማራው ልዩ ሃይል በአዲ ምስኖ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ብዛት ያላቸው ጥይቶችን በማከማቸት የአካባቢውን ህ…

በራያ ግንባር ተደጋጋሚ ሽንፈትን እየተከናነበ የሚገኘው ከሃዲው ሕወሓት ያሰማራው ልዩ ሃይል በአዲ ምስኖ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ብዛት ያላቸው ጥይቶችን በማከማቸት የአካባቢውን ህ…

በራያ ግንባር ተደጋጋሚ ሽንፈትን እየተከናነበ የሚገኘው ከሃዲው ሕወሓት ያሰማራው ልዩ ሃይል በአዲ ምስኖ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ብዛት ያላቸው ጥይቶችን በማከማቸት የአካባቢውን ህብረተሰብ ያስቆጣ ተግባር መፈፀሙ ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 19 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በራያ ግንባር ለግዳጅ በተሰለፈው ኃይል ተደጋጋሚ ሽንፈትን እያስተናገደ የሚገኘው ዘር አጥፊው ሕወሓት ለጥፋት ያሰማራቸው የልዩ ሃይል አባላት በአዲ ምስኖ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያንን እንደምሽግ በመጠቀም እንዲጎዳ አድርገዋል። አቶ በሀይሉ በርኸ የተባሉ የአካባቢው ነዋሪ በቤተ ክርስቲያኑ ውስጥም ብዛት ያላቸው ጥይቶችን በማከማቸት የአካባቢውን ህብረተሰብ ያስቆጣ አረመኔያዊ ተግባር ፈፅሟል ሲሉ ገልፀዋል። አቶ በሀይሉ ሲቀጥሉ “ቤተ ክርስትያን ውስጥ የመድፍ ጥይት እና ቢ ኤም መሳሪያ አምጥተው አስቀመጡ፤ለምን? ስንላቸው ቤተክርስትያኑ አይመታባችሁም ከተመታም የጥይት ሳጥን እንሰጣችሁና እሱን ሸጣችሁ ታስጠግኑታላችሁ አሉን” ሲሉ የሕወሓትን ገመና አጋልጠዋል። “ቤተ ክርስትያኑ ፈርሷል ውስጡ ያለው ፅላትም ይኑር አይኑርም የምናውቀው ነገር የለም ፣ ወያኔ ለሃይማኖት እኩልነት እቆማለሁ ሲል የነበረ ድርጅት ዛሬ ግን ስጋወደሙ የምንቀበልበትን የእምነት ቦታ አርክሶብናል” ሲሉ ነው አቶ በሀይሉ በሃዘንና በቁጭት ስሜታቸውን ያጋሩት። ሕወሓት ገና ከ1976 ጀምሮ በጫካ ሆኖ ሴራ በመዶለት፣ በማኒፌስቶው ጭምር በማካተት ፀረ አማራ፣ ፀረ ኢትዮጵያና ፀረ ኦርቶዶክስ አቋም ይዞ በመነሳት በአደባባይ አከርካሪውን ሰብረነዋል ነማለት የሚናገሩ መሪዎች ስብስብ መሆኑ ይታወቃል። ዛሬ ላይ ሲፈፅመው የኖረው ግፍና በደል በዝቶ፣ ክህደት፣ እብሪትና ድንቁርናውም ጫፍ ላይ ደርሶ በአገር አቀፍ ደረጃ እየተወሰደበት ባለው ህግ የማስከበር ጠንካራ እርምጃ ወደ መቃብር እየወረደ መሆኑ ይታወቃል። ዘገባውን ለማጠናቀር ዋልታ ሚዲያን በምንጭነት ተጠቅመናል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply