You are currently viewing በርሃብ አለንጋ እየተሰቃዩ መሆናቸውን ተፈናቃዮች ተናገሩ፡፡ የአማራ ሚዲያ ማእከል   የካቲት 19/2015 ዓ/ም      አዲስ አበባ በአማራ ክልል በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር በአበርገሌ…

በርሃብ አለንጋ እየተሰቃዩ መሆናቸውን ተፈናቃዮች ተናገሩ፡፡ የአማራ ሚዲያ ማእከል የካቲት 19/2015 ዓ/ም አዲስ አበባ በአማራ ክልል በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር በአበርገሌ…

በርሃብ አለንጋ እየተሰቃዩ መሆናቸውን ተፈናቃዮች ተናገሩ፡፡ የአማራ ሚዲያ ማእከል የካቲት 19/2015 ዓ/ም አዲስ አበባ በአማራ ክልል በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር በአበርገሌ ወረዳ በ03 ቀበሌ በበልታርፍ ከተማ መጠላያ ካምፕ ተጠልለው የሚገኙ የወረዳው ተፈናቃይ ማኅበረሰብ የዕለት ምግብ አጥተን በርሃብ አለንጋ እየተሰቃየን ነው ሲሉ ተናገሩ፡፡ በከባድ መሳሪያ ምክንያት ቤቴ በመደብደቡ ሕይወቴን ለማትረፍ ከቀዬ ተፈናቅየ የደረሱ ሰብሎችን ሳልሰበስብ በትኜ መጣሁ የሚሉት በ03 ቀበሌ የኮታርፍ ጎጥ ነዋሪ የሆኑት ወ/ሮ ቲቱ አየለ ከመጠለያ ካምፑ ከተጠለልኩ ግማሽ ዓመት ሁኖኛል ነገር ግን ለምኝታ የምትሆን ምንጣፍ ውጭ ያገኘሁት የምግብ አቅርቦትም ሆነ መገልገያ ንብረት የለም ብለዋል፡፡ አክለውም በጣም ስንቸገር እና በርሃብ ምክንያት በሽታ ላይ ስንወድቅ መጠለያ ካምፑን ለቀን ሰው ካለበት ከከተማው እየተጠጋን ለምነን እየበላን እንገኛለን ሲሉ በርሃብ ክፉኛ መጎዳታቸውን ተናግረዋል፡፡ሌላው ወጣት ታዘዘ በሪሁን በበኩላቸው እኛ የመጣነው በሰላም እጦትና በርሃብ ምክንያት ነው፤ ነገር ግን የምናርፍበትና የምንተኛበት ካምፕ ከመሰራቱ ውጭ ሌላ ያገኘነው ጥቅም የለም፡፡ በእውነት እኛ እሳካሁን ያለነው ከመከላከያውና ከልዩ ኃይሉ በምናገኘው ደረቅ ኮቸሮ ነው፤ ይህን ባናገኝ በርሃብ አልቀን ነበር ሲሉ የዕለት ጉርስ አጥተው መሰቃየታቸውን ገልጸዋል፡፡ ተፈናቃዮቹ ሲናገሩ ረጂ ድርጅቶችን በምጠይቅበት ጊዜም ቦታው የስጋት ቀጠና ነው እስከዛ ድረስ ማን ይመጣል የሚል ምላሽ ነው የሚሰጠን አሁን ግን ሕዝቡ በዚህ በሞቃታማ ቦታ ላይ የሚተኛው ፍራሽ አጥቶ ዲንጋይ ተተንተርሶ ነው አክለውም በአሁኑ ሰዓት በመጠለያ ካምፑ ከ01፣ ከ03ና ከ04 ቀበሌዎች ተፈናቅሎ የመጣ ከ2ሺ 8መቶ በላይ የሚሆን ተፈናቃይ ይገኛል ያሉት አስተባባሪው የወረዳው ሆነ የዞኑ ምግብ ዋስትና እስካሁን ምንም ዓይነት ድጋፍ ስላላደረገ ለተቸገረው ህዝብ ትኩረት ቢስጥ ጥሩ ነው ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ በአጠቃላይ በዋግኽምራ ዞን እስከ አሁን ድረስ በህወሓት ታጣቂዎች የተያዙት በፃግብጂ እና አበርገሌ ወረዳወች የታጣቂያቸው ማሰልጠኛ ቦታውን በማድረጋቸው በህዝቡ ላይ ከፍተኛ በደል እየፈፀሙባቸው ሲገኝ ይሄንን መከራ ለማሳለፍ ወደ ሰቅጣ ከተማ 90,000 /ዘጠና ሺ ተፈናቃዮች / ለከፋ እርሃብ በመጋለጣቸው ድጋፍ እንዲደረግላቸው ጥሪ አቅርበዋል። ምንጭ አሻራ

Source: Link to the Post

Leave a Reply