
በርካታ ኢትዮጵያውያን ለንግድ፣ ለሥራ፣ ለህክምና፣ ለትምህርት እንዲሁም ለመዝናናት የሚጓዙባት ቱርክ በከባድ ርዕደ መሬት ተመትታ በሺዎቹ የሚቆጠሩ ዜጎቿ ላይ አደጋ ደርሷል። የተጎዱ ሰዎች ቁጥርም ሊጨምር እንደሚችል ተሰግቷል። ይህ ቱርክን ያጋጠመው የተፈጥሮ አደጋ በአገሪቱ ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ላይ ያስከተለው ጉዳት ይኖር ይሆን? አሁን ያሉበትስ ሁኔታ ምን ይመስላል በሚል ቢቢሲ የተወሰኑትን አናግሯል።
Source: Link to the Post