በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚደርስ ጥቃት እንዲቆም ተጠየቀ

https://gdb.voanews.com/09410000-0a00-0242-ef73-08dad979397b_tv_w800_h450.jpg

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ በሐዋሳ ከተማ በተከበረው በ17ኛው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን በዓል ላይ ተገኝተው ኢትዮጵያ ጠንካራ የፀጥታ ኃይል ያላት ሀገር መሆኗን ገልፀዋል።

“ኢትዮጵያውያን ሀገር ለማወክ ለሚሰራጩ የግጭትና የጥላቻ አጀንዳዎች ጆሮ ባለመስጠት አብሮነታችንን  አጠናክረን መቀጠል አለብን” ሲሉም ተደምጠዋል።

በንግግራቸው ላይ ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል ወለጋ ዞን በሰላማዊ ሰዎች  ላይ ተፈፀመ ስለተባለው ጥቃትም ሆነ ጥቃት ያደርሳሉ በሚባሉ ቡድኖች ላይም በቀጥታ የተናገሩት ነገር የለም።

በሌላ በኩል የሰላማዊስ  ግድያ፣ የአካል ጉዳትና መፈናቀል የፌዴራል መንግሥቱን እንዲያስቆም ዜጎች ደህንነታቸው ተጠብቆ በሰላም እንዲኖሩ የተለያዩ ፖለቲካ ፓርቲዎችና ሲቪክ ማኅበራት እየወተወቱ ይገኛሉ።

በኢትዮጵያ በንፁሃን ላይ የሚደርሰውን ጥቃት መንግሥትና ሕዝብ ተባብረው እንዲያስቆሙ የጠየቁና ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየታቸውን የሰጡ ፤ መንግስትና ህዝብ ጊዜ ሳይሰጡ መገዳደልን ማስቆም እንደሚገባቸው አሳስበዋል።

/ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/ 

Source: Link to the Post

Leave a Reply