You are currently viewing በሰላም ሚኒስትር በኩል የስራ እድል ይፈጠርላችኋል በሚል ለ45 ቀናት ሰልጥነው የተመረቁና ለ10 ወራት በበጎ ፈቃድ ተሰማርተው ግዳጃቸውን እንደተወጡ የተናገሩት ወጣቶች የተገባልን ቃል ባለመፈ…

በሰላም ሚኒስትር በኩል የስራ እድል ይፈጠርላችኋል በሚል ለ45 ቀናት ሰልጥነው የተመረቁና ለ10 ወራት በበጎ ፈቃድ ተሰማርተው ግዳጃቸውን እንደተወጡ የተናገሩት ወጣቶች የተገባልን ቃል ባለመፈ…

በሰላም ሚኒስትር በኩል የስራ እድል ይፈጠርላችኋል በሚል ለ45 ቀናት ሰልጥነው የተመረቁና ለ10 ወራት በበጎ ፈቃድ ተሰማርተው ግዳጃቸውን እንደተወጡ የተናገሩት ወጣቶች የተገባልን ቃል ባለመፈጸሙ ለከፋ ሁለንተናዊ ችግር ተዳርገናል ሲሉ አማረሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 2 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በሰላም ሚኒስትር በኩል የስራ እድል ይፈጠርላችኋል በሚል ለ45 ቀናት ሰልጥነው የተመረቁና ለ10 ወራት በበጎ ፈቃድ ተሰማርተው ግዳጃቸውን እንደተወጡ የተናገሩት ወጣቶች ቀጥታ ወደ ስራ እንደሚሰማሩ በሰላም ሚኒስትር አመራሮች በኩል ቃል ተገብቶላቸው እንደነበር ይናገራሉ። እንደአብነት ሲጠቅሱም ከሰላም ሚኒስትር አስማ ረዲ_”በአንድ ዓመት ውስጥ 3 ሚሊዮን ወጣቶችን ስራ በምናሲዝበት ሀገር ውስጥ እንዴት አስር ሺህ ወጣቶችን ስራ አናሲይዝም ብላችሁ ታስባላችሁ? እንቀጥራችኋለን” ብለው በዙም ውይይት ላይ ስለመናገራቸው አውስተዋል። ይሁን እንጅ የተቋሙ አመራሮች የገቡትን ቃል ባለማክበራቸው ለከፋ ሁለንተናዊ ችግር ተዳርገናል ሲሉ እያማረሩ ነው። በተዳጋጋሚ አቤቱታ ብናቀርብም ሰሚ አላገኘንም የሚሉት የዩኒቨርስቲ ምሩቃን ይባስ ብሎ ለጥያቄያችን መልስ የሚሰጥ አካል መኖር አለበት በሚል በሰላማዊ ሰልፍ ቅሬታችን ለማሰማት ብንወጣም የጅምላ እስር እና ወከባ ገጥሞናል ሲሉ ገልጸዋል። እነዚህ የዩኒቨርስቲ ምሩቃን እንደሚሉት በ2013 ዓ/ም ለ45 ቀናት በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ሰልጥነው የካቲት 27/2013 በአዲስ አበባ ከተማ የወዳጅነት አደባባይ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ እና ሌሎች በየደረጃው ያሉ ባለስልጣናት በተገኙበት ተመርቀዋል። አለባችሁ የተባሉትን በበጎ ፈቃደኝነት የማገልገል የ10 ወር ግዳጃቸውንም የተወጡ ብሄራዊ በጎ ፈቃድ የማህበረሰብ አገልግሎት ተሳታፊዎች መሆናቸውን ገልጸዋል። በተገባልን ቃል መሰረት የስራ እድል ፈጠራው አልተመቻቸልንም የሚሉት አቤቱታ አቅራቢዎች ከመመረቃችን በፊት የስራ እድል ፈጠራ ወይም የቅጥር ፎርም የመሰለ ነገር አስሞልተውን ነበር ይላሉ። የሲዳማ ክልል ተመራቂዎችን ኦፊሻሊ እያስተናገዳቸው ይገኛል፤ በኦሮሚያም በውስጥ እየተሰራበት እንደሆነ እናውቃለን የሚሉት ወጣቶቹ አማራ ክልል ላይ ግን ከፍተኛ ችግር አለ ብለዋል። በቅርቡ ከ3 ነጥብ በላይ ያላቸው በሚል ለኢሚግሬሽን 100 ልጆችን ብቻ መልምለው የወሰዱ መሆናቸውን ጠቅሰው አካሄዱ ሌሎችን ዝም ለማሰኘትና በተስፋ እንዲጠብቁ ለማድረግ እንደሚሆን ይገልጣሉ፤ በምልመላ መስፈርቱም አይስማሙም። 3.8 ውጤት ይዞ ያልተመለመለ፤ በተቃራኒው 3.08 ውጤት እያለው ተመልምሎ የገባ መሆኑን በመጥቀስ አሰራሩ ግልጽነት የጎደለው ነው ብለዋል። በወር ይሰጥ የነበረው 3,276 ብር ግዴታችሁን ተወጣችኋል በሚል ሰርትፊኬት በመስጠት ደመወዝ ከተቋረጠ ሁለት ወር ሆኖታል ሲሉም አክለዋል። ከሰላም ሚኒስተር የተጻፈው የምስጋና እና የእውቅና ምስክር ወረቀትም ስራ የሚያሲዝ ሳይሆን ማንኛውም አካል ሊጽፈው የሚችል ነው በሚል በዞንና በወረዳ ተቀባይነት የለውም ብለዋል። ይህን አካሄድ በማውገዝ የካቲት 28/2014 ከጠዋቱ 3 ሰዓት አካባቢ እስከ 200 የሚደርሱ ወጣቶች በመስቀል አደባባይ ተገናኝተው ወደ ሰላም ሚኒስትር እና ጠ/ሚኑስትር ጽ/ቤት ለአቤቱታ ለማቅናት እየተዘጋጁ ሳለ እስርና ወከባ ተፈጽሞብናል ሲሉ ወቅሰዋል። ይኽውም መጀመሪያ ላይ ማንነቱን የማናውቀው ሰው በቴሌግራም ገጻችን ገብቶ እያንዳንዱን እንቅስቃሴ በመከታተል በኦሮሚኛና በአማርኛ በመጻፍ ያስፈራራን ነበር ብለዋል። በመስቀል አደባባይ እያለን አንድ ሲቪል የለበሰ ሰው መጣና ምን እየሰራችሁ ነው ብሎ ሲጠይቀን አቤቱታ ለማቅረብ እየሄድን መሆኑን ከመንገራችን በስልኩ መሴጅ ተጻጽፎ ወዲያውኑ 4 ፓትሮል አስመጣ ይላሉ። 72 የምንሆነውን በ4 ፓትሮል እንድንጫን በማስገደድነበአዲስ አበባ ወደማናውቀው ፖሊስ ጣቢያ ወሰደን፤ ሌሎች 25 የሚሆኑ በጎ ፈቃደኞችንም በአንድ ፓትሮል ጭነው ወደ ሌላ ጣቢያ ወሰዷቸው ሲሉ ተናግረዋል። በድምሩ 97 ወጣቶች መታሰራቸውን የገለጹ ሲሆን ይሁን እንጅ በእለቱ ከምሽቱ 2:30 አካባቢ እንዳይደግማችሁ በሚል ሁሉንም ካስፈራሩ በኋላ 5 ቅሬታ አቅራቢዎችን በማስመረጥ እንደለቀቋቸው አውስተዋል። ከመካከላቸው 2 ልጆችን ቀስቃሽ ናቸው በሚል መርጠው በድብቅ በመውሰድ ሌላ ጣቢያ 2 ቀን ካሰሩ በኋላ አስፈራርተው ለቀቋቸዋል ያሉት ወጣቶቹ የ1 ሽህ ብር ዋስ ቢጠየቁም የለንም በማለታቸው እንዲሁ ተፈተዋል ብለዋል። ከ72ቱ 5 ልጆች ጥያቄ እንዲያቀርቡ የተመረጡ ሲሆን እነሱም የካቲት 29/2014 ወደ ጠ/ሚ/ጽ/ቤት ሲሄዱም አላገኟቸውም በኢሜል ግን ደብዳቤ አስገብተዋል፤ ብልጽግና ጽ/ቤት ሄደውም በስብሰባ ምክንያት አላገኟቸውም። በመጨረሻም ወጣቶቹ የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት በአስቸኳይ ፍትህ እንዲሰጧቸው ጠይቀዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply