በሰላም እጦት ሰዎች የሚሰቃዩባት መተከልና አካባቢዉ ሰላም ያገኝ ዘንድ ምን አየተሰራ ይሆን? በመተከል እና በአማራ ክልል ወረዳዎች የሰላም ምክክር መድረክ መካሄዱን ሰምተናል ።አራት ዓመታት…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/M-oFuz8PJ2PNCm10no9CNWElORtq0C1mgeh8JE8hzIpu5NLXkQbDEv3HH41fbD1Nk0kJXQWX5PRLX8bNS0UQEJvJDTS0tf6FT_azUGECj1uJdRiKiCSjV9OcE2tGZv-NGWA5GMjsj3ww_F3J7DuRYj79fGHA-U_uhrwCeMJKuOSkPsQ-eDqSIqNAU0p9p6g7MVo7EfpEdqZCBy2iqwUHTvc4gTWhn98cUegqLaAN_mATQfc4RKo8Y_Ct0bV-s5six_XhpP2GcZF47JJwtEYJFkWa0BcbWQfzp-IOLCy0B4r3q-RU2pdVr0BxOxLYkz4mU2atp93Wqp6v3aavSJoJGA.jpg

በሰላም እጦት ሰዎች የሚሰቃዩባት መተከልና አካባቢዉ ሰላም ያገኝ ዘንድ ምን አየተሰራ ይሆን?

በመተከል እና በአማራ ክልል ወረዳዎች የሰላም ምክክር መድረክ መካሄዱን ሰምተናል ።

አራት ዓመታትን ያስቆጠረው የመተከል ዞን የሰላም መደፍረስ ወደ ፍፁም ሰላም እንዲመለስ፣ በመተከል እና በአማራ ክልል አጎራባች ወረዳዎች በትናንትናው ዕለት የምክክር መድረክ ተካሂዷል ።

የጓንጓ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ብርሃኑ መኮንን ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት፤ ከሁሉም የመተከል ዞን ወረዳዎች እና የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ወረዳዎች የተውጣጡ የእምነት አባቶች፣የሀገር ሽማግሌዎች፣የፖለቲካ አመራሮች እና በአጠቃላይ ከ500 በላይ እንግዶች ተሳትፈውበታል።

ወረዳዎቹ ከዚህ በፊት ብዙ ተፈናቃዮችን ያስተናግዱ እንደነበር እና በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የችግሩ ገፈት ቀማሽ እንደነበሩ የገለፁት ኃላፊው፣ አሁን የነበረውን ግጭት ወደ ጎን ትተው ለእርቅ መስማማታቸውን ገልፀዋል።

ከሁለቱም ወገን እንደቀድሞው ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንዲኖር መግባባት ላይ የተደረሰ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን፣ በቦታው ያሉ ልዩ ሀይሎች፣ መከላከያን ጨምሮ እንዲሁም ጥምር የፌዴራል ፖሊስ ሃይል ሀላፊነት እንዳለባቸውም ተነስቷል ።

ከዚህ በፊት ሸፍተው በጫካ የነበሩ የጉሙዝ ብሔረሰብ ተወላጆች እጃቸውን በመስጠት ትጥቅ ፈትተው፤ በባህላቸው መሠረት ዕርቅ ፈፅመው ከማህበረሰቡ ጋር መቀላቀላቸውንም አቶ ብርሃኑ ነግረውናል።

በእስከዳር ግርማ

ግንቦት 08 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply