በሰሜኑ የኢትዮጵያ ጦርነት ከተቋረጡት የመንገድ ፕሮጀክቶች መካከል 39 ያህሉ ወደ ግንባታ ማስገባት አልተቻለም ተባለ።ከሁለት አመት በፊት በሰሜኑ የሃገራችን ክፍል በነበረው ጦርነት ምክንያት…

በሰሜኑ የኢትዮጵያ ጦርነት ከተቋረጡት የመንገድ ፕሮጀክቶች መካከል 39 ያህሉ ወደ ግንባታ ማስገባት አልተቻለም ተባለ።

ከሁለት አመት በፊት በሰሜኑ የሃገራችን ክፍል በነበረው ጦርነት ምክንያት 64 ግዙፍ ፕሮጀክቶች ከፍተኛ ውድመት እንደደረሰባቸው ተነግሮ ነበር።

የኢትዮጵያ የመንገድ አስተዳደር ጉዳት ደርሶባቸው ከነበሩ መንገዶች መካከል 15 ያህሉን አገልግሎት እንዲሰጡ ተደርጓል ብሏል።

የአስተዳደሩ ዋና ዳሬክተር አቶ መሃመድ አብዱራህማን ውድመት የደረሰባቸው መንገዶች አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ ጊዜ እንደሚወስድ ተናግረው ፕሮጀክቶቹን ለማስጀመር አዲስ ጨረታ ማውጣት አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።

ከፕሮጀክቶች መካከል በአሁኑ ወቅት ግንባታቸው የቀጠለው 15 ብቻ መሆናቸውን የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ አብዱራህማን ባቀረቡት ሪፖርት ተናግረዋል።

ከተቋረጡት የመንገድ ፕሮጀክቶች ውስጥ 39 የሚሆኑት “ከፍተኛ የሆነ ጉዳት” ስለደረሰባቸው፤ በድጋሚ ወደ ጨረታ ሂደት እንዲገቡ መደረጋቸውን ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።

አቶ መሐመድ ይህን ያሉት የተቋረጡ የመንገድ ፕሮጀክቶችን በተመለከተ ከፓርላማ አባላት ለቀረቡ ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ ነው።

ጥያዎቹ በተወካዮች ምክር ቤት አባላት የተነሱት፤ የከተማ እና መሰረት ልማት ሚኒስቴር የ2016 በጀት ዓመት የስድስት ወራት አፈጻጸም ሪፖርት ባቀረበበት ላይ ነው።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

ኤትዩ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ጥር 22 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Source: Link to the Post

Leave a Reply