በሰሜኑ ጦርነት ጉዳት የደረሰበት የአክሱም አየር ማረፊያ በመጪዉ ሰኔ አገልግሎት መስጠጥ ይጀምራል ተባለ፡፡በትግራይ በነበረው ግጭት ውድመት ደርሶበት የነበረው የአክሱሙ የአፄ ዮሐንስ አ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/WuLEpXPND-ftKtbVKy0vfpET2knz7Cs2_Jux0qZ69gCvGwRN8esXZrN_kEDDGV8o3ZN7cyKLZlkK6cleNVq0JQT2jt817xyF-mKUyOiiPdrDeBXIRo-bHivfsjAhFY-_FAMiBktgjLTScbydpJYZgGDhLCc2cSy-KakrjRiRxk1teJpIjNvoNRsPHb7oxHqKUnlbTM0u6VJpGjgBuPD_UDGg3TEVPrW37Kg8zAd4wRrx347dT_zEseJXJLqQRpAjcqn4kGtEEs00Rq73WrFudjTzQuCCgTH57KXogj4bROhRXzaE1y7VA_3lZ9h7E9lH38x9IrMuRsPXTShqvmSSAQ.jpg

በሰሜኑ ጦርነት ጉዳት የደረሰበት የአክሱም አየር ማረፊያ በመጪዉ ሰኔ አገልግሎት መስጠጥ ይጀምራል ተባለ፡፡

በትግራይ በነበረው ግጭት ውድመት ደርሶበት የነበረው የአክሱሙ የአፄ ዮሐንስ አራተኛ አየር መንገድ የእድሳት ስራ በመጪዉ ሰኔ 2016 ዓ.ም አገልግሎት ይሰጣል ተብሏል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው መልሶ ግንባታዉ በጥሩ ሁኔታ ላይ እንዳለ ገልፀዋል።

ብዙ ጉዳት እንደደረሰበት እና እድሳቱ ሳይጀመር ብዙ ጊዜ እንደፈጀ የሚናገሩት አቶ መስፈን አሁን ላይ እድሳቱ እየተሰራ እንደሆነ በማንሳት በመዘግየቱም ይቅርታ ጠይቀዋል፡፡

የአክሱም ቱሪዝም ቢሮ ሀላፊ አቶ ገብረ መድህን ፍጹም ብርሃን በበኩላቸው እድሳቱን ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነዉ ብለዋል፡፡

ሀላፊው የአየር ማረፊያው መታደስ ለአክሱም ቱሪዝም ትልቅ አበርክቶ እንዳለውም ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለመልሶ ግንባታዉ ከ200 ሚሊዮን በላይ በጀት እንደመደበም ሰምተናል፡፡

በለአለም አሰፋ

መጋቢት 12 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
Twitter https://twitter.com/EthioFM
YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos
Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcas

Source: Link to the Post

Leave a Reply