በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት በደብረ ብርሃን ከተማ አጼ ዘርዐ ያዕቆብ አደባባይ በኅልውና ዘመቻ ለሀገርና ለወገን በመዋደቅ ለተሰው ልዩ ልዩ የፀጥታ አካላት ለሦሥት ቀናት ጸሎተ ፍትሐትና ጸሎተ…

በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት በደብረ ብርሃን ከተማ አጼ ዘርዐ ያዕቆብ አደባባይ በኅልውና ዘመቻ ለሀገርና ለወገን በመዋደቅ ለተሰው ልዩ ልዩ የፀጥታ አካላት ለሦሥት ቀናት ጸሎተ ፍትሐትና ጸሎተ ምሕላ ተካሄደ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 9 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በነገሥታቱ መናገሻ ደብረ ብርሃን በታላቁ ንጉሠ ነገሥት ቆስጠንጢኖስ ዘኢትዮጵያ መፍቀሬ ሃይማኖት አጼ ዘርዐ ያዕቆብ አደባባይ ለሦሥት ቀን በብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከትና በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሊቀ ጳጳስ መሪነት ሲካሄድ ጸሎተ ፍትሐቱና ጸሎተ ምሕላው በታላቅ ድምቀት ለሦሥት ቀናት ሲካሄድ ቆይቷል። በጸሎተ ፍትሐትና በጸሎተ ምሕላ መርሐ-ግብሩ ዓላማ መረት ስለሀገራችን ወቅታዊ ችግር ጸሎት የደረገ ሲሆን የሁሉም አድባራት አስተዳዳሪዎች ፣ መዘምራንና ካህናት በተገኙበት ለሀገራቸውና ለወገናቸው ሲሉ ሕይወታቸውን ለሰጡ ወገኖቻችን ጸሎተ ፍትሐት ተደርጓል። ይኽ ጸሎተ ፍትሐትና ጸሎተ ምሕላ መርሐ-ግብር በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ የከተማዋ ነዋሪዎች ምእመናን በተገኙበት ለ3 ቀናት የተካሄደ ሲሆን “ይኽችን ከተማ አድናት ዘንድ እጋርዳታለሁ” በሚል ርእስ ያዘኑና የተከዙ የተቸገሩና በመከራ ያሉ የተራቡ የተጠሙ እንዲጽናኑ ሰፊ ትምህርተ ወንጌል በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ በክቡር መጋቤ ሐዲስ ነቅዐ ጥበብ አባቡ ተሰጥቷል ሲል የዘገበው የሰሜን ሸዋ ኮሚዩኒኬሽን ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply