በሰሜን ሸዋ አጣዬ አካባቢ በአማራ ልዩ ኃይል ላይ የደረሰዉን ገዳት አስመልክቶ ከአማራ ህዝባዊ ኃይል (ፋኖ) የተሰጠ መግለጫ:- “””””””””””””””””””'''''”””””””””””””””…

በሰሜን ሸዋ አጣዬ አካባቢ በአማራ ልዩ ኃይል ላይ የደረሰዉን ገዳት አስመልክቶ ከአማራ ህዝባዊ ኃይል (ፋኖ) የተሰጠ መግለጫ:- “””””””””””””””””””””'”””””””””””””””””””‘”””””””'”””””””’ የአማራ ህዝብ መከታ መሆኑን በተደጋጋሚ በተግባር ያረጋገጠዉ የአማራ ልዩ ኃይል ባልተሟላ ሎጅስቲክስ እና አመራር ውስጥ ሆኖ የአማራን ህዝብ ከጥፋት ለመታደግ መራር መስዋዕትነት በመክፈል ላይ መሆኑ ይታወቃል። ሐምሌ 03 እና 04 ቀን 2014 ዓ.ም በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም እ… ወረዳ በአማራ ህዝብ ላይ የተከፈተውን ጥቃት በመከላከል ላይ እያሉ በተቀነባበረ ሴራ ምክንያት ቁጥራቸው በርከት ያለ የልዩ ኃይል አባላት ተሰውተዋል። በርካቶችም ከባድ እና ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል። የአማራ ህዝባዊ ኃይል (ፋኖ) በክልሉ ውስጥ በተደራጀ ታጣቂ አማካኝነት በአማራ ልዩ ኃይል አባላት ላይ በደረሰው ጉዳት መሪር ሀዘን የተሰማው መሆኑን ይገልፃል። መላው የልዩ ኃይላችን አመራር እና አባላት ውድ ህይወታችሁን የምትሰጡለት የአማራ ህዝብ ላይ የተደቀነበትን የህልዉና አደጋ ለመቀልበስ የምታደርጉትን ተጋድሎ እያደነቅን የአማራ ብልፅግና የሚባለውን ድርጅት ተጠቅመው ሊያጠፋፉን የሚፈልጉ ዋነኞቹ ጠላቶቻችን እናንተን ከፋኖ ወንድሞቻችሁ ጋር በማጋጨት የአማራዉን ኃይል በመበተን ህልማቸውን ለማሳካት የሚያደርጉትን ጥረት እንድትረዱ እና ከቆማችሁለት ዓላማ ውጭ ስምሪት የሚሰጣችሁን የፖለቲካ አመራር በቃህ እንድትሉት፤ ባልተሟላ የመረጃ፣ የአመራር እና የሎጅስቲክስ አቅርቦት ለአደጋ እያጋለጣችሁ ያለዉን የፖለቲካ አመራር ልዩ ኃይሉን ለከፋ አደጋ ከሚያጋልጥ ስዉር ሴራው እንዲታቀብ ወታደራዊ አካሄዱ በሚፈቅደው አሰራር መሰረት በየአደረጃጀታችሁ እንድትታገሉት ጥሪ እናስተላልፋለን። በአካባቢው ያላችሁ የአማራ ፋኖ አባላት ልዩ ኃይሉ ላይ ከሆነውም የከፋ ጉዳት እንዳይደርስ ላደረጋችሁት ተጋድሎ ከፍተኛ አድናቆት ያለን መሆኑን እየገለፅን ሁሉም የፋኖ አመራር እና አባላት እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ ጥበብ እና ብስለት የተሞላበትን አካሄድ በመከተል ከልዩ ኃይላችን ጋር ስምሪት ጋር ተያይዞ ጠላቶቻችን የሸረቡልንን የመጠፋፋት ሴራ እንድናከሽፍ ጥሪ እናቀርባለን። በመጨረሻም መስዋዕትነት ለከፈሉ የልዩ ኃይላችን ቤተሰቦች መፅናናትን እንመኛለን። አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ! የአማራ ሕዝባዊ ኃይል (ፋኖ) ሐምሌ 05 ቀን 2014 ዓ.ም ባሕርዳር-ኢትዮጵያ

Source: Link to the Post

Leave a Reply