በሰሜን ሸዋ ዞን ሲያደብር እና ዋዩ የደነባ ከተማ ነዋሪዎች በመጠጥ ውሀ እጦት እየተቸገሩ መሆናቸውን ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 11 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ…

በሰሜን ሸዋ ዞን ሲያደብር እና ዋዩ የደነባ ከተማ ነዋሪዎች በመጠጥ ውሀ እጦት እየተቸገሩ መሆናቸውን ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 11 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በሰሜን ሸዋ ዞን ሲያደብር እና ዋዩ የደነባ ከተማ ነዋሪዎች በመጠጥ ውሀ እጦት እየተቸገሩ መሆናቸውን ገልፀዋል። በደነባ ከተማ ሀለሐመ በተባሉ ዞኖች ውሀ ብዙ ጊዜ እንደማይጠፋ የተናገሩት የደነባ ከተማ ነዋሪ በተለይ ግን በጊዮርጊስና ባታ ሰፈሮች በቂ የመጠጥ ውሀ ማግኘት አልተቻለም ብለዋል። ለችግሩ እልባት የሚሰጥ አካል አላገኘንም ያሉት ነዋሪው ቢያንስ በየሁለት ሳምንቱ እንኳ የንፁህ መጠጥ ውሀ ማግኘት ባለመቻሉ በጣም ተቸግረናል ብለዋል። ውሀን የሚገፋ የመብራት ኃይል ትራንፎርመሩ በመቃጠሉ ነው የሚል ምክንያት ከመስጠት ያለፈ ለችግሩ እልባት የሚሰጥ አካል አላገኘንም ነው ያሉት። እንደአብነት በጊዮርጊስ ሰፈር በፈረቃ ተብሎ አንድ ጊዜ በ10ኛ ቀኑ፣ሌላ ጊዜ ደግሞ በ25ኛ ቀኑ ውሀ በሌሊት ለተወሰነ ሰዓት የተለቀቀላቸው መሆኑን ያወሱት ነዋሪው ለችግሩ የሚመለከተው የመንግስት አካል አስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጥበት ጠይቀዋል። የንፁህ መጠጥ ውሀ ተጠቃሚ እየሆን አይደለም፣ የችግሩን ስፋት አመራሩ እያወቀው ለምን መፍትሄ አይሰጡም የሲያደብር እና ዋዩ ወረዳ የውሀ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ እታገኝን ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ስልካቸው ባለመስራቱ ለጊዜው አልተቻለም። የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘውዱ ሰይፉ በበኩላቸው የንፁህ መጠጥ ውሀ ችግር እያጋጠመ መሆኑን አምነው በተለይ ደግሞ ጊዮርጊስ እና ባታ ሰፈሮችን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎችም ችግሩ መኖሩን ጠቅሰዋል። ከኮሮና አንጻርም ለአንዳንድ ተቋማት የውሀ አቅርቦት ለማሟላት ችግር እያጋጠመ መሆኑን ጠቅሰው ለችግሩ መፍትሄ እንዲሰጥ እየሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል። ለጊዜው በዙሪያ ያሉ መለስተኛ ጉድጓዶችን ለመጠቀምና በፈረቃ ለማድረስ ቢሞከርም እሱም ውጤታማ አለመሆኑን የገለፁት አስተዳዳሪው ከሰሜን ሸዋ ዞን መስተዳድርና የውሀ መምሪያ ጋር ተነጋግረንበታል ብለዋል። በመሆኑም ክሬን እና ሌሎች አስፈላጊ ግብአቶችን በማስመጣት በቅርብ ጊዜ ምንአልባትም በሳምንት ውስጥ ችግሩን ለመፍታት እየተሰራ መሆኑን ነው አቶ ዘውዱ ያስታወቁት።

Source: Link to the Post

Leave a Reply