በሰሜን ሸዋ ዞን በሞረትና ጅሩ ወረዳ በአስገድዶ መድፈረና በጠለፋ ወንጀል የተጠረጠሩት ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ     ጥር 8 ቀን 2013 ዓ.ም          አ…

በሰሜን ሸዋ ዞን በሞረትና ጅሩ ወረዳ በአስገድዶ መድፈረና በጠለፋ ወንጀል የተጠረጠሩት ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 8 ቀን 2013 ዓ.ም አ…

በሰሜን ሸዋ ዞን በሞረትና ጅሩ ወረዳ በአስገድዶ መድፈረና በጠለፋ ወንጀል የተጠረጠሩት ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 8 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የሞረትና ጅሩ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ምክትል ኮማንደር ወጋየሁ ቦጋለ እንደገለጹት በቀን 24/04/2013 ከቀኑ 8፡00 ሰዓት አካባቢ ከወላጅ አባቷ ጋር ከእነዋሪ ከተማ ወደ መኖሪያ ቀያቸው የወሎ ቀበሌ በመመለስ ላይ ባሉበት ወቅት የየወሎ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አቶ ጌታው ሽትዬ ከተባባሪ ጓደኛው ከአቶ ሞገስ ባቡሽ ጋር በመሆን አባቷን በሽጉጥ በማስፈራራት የ14 አመት ልጅ በመጥለፍ በመርሃቤቴ ወረዳ ሁለት ሽጉጥ በመያዝ ተሸሽገው ነበር። በዚህ ወቅት ከመርሃቤቴ ወረዳ ጋር በጋራ በመቀናጀት ፖሊስ ባደረገው ክትትል በቁጥጥር ስር ውለው የሞረትና ጅሩ ወረዳ ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ክፍል ጉዳዩን በተገቢው መንገድ ካጣራ በኳላ ለአቃቢ ህግ ጽ/ቤት በመላክ ክስ ተመስርቶ ብይን መሰጠቱን ገልፀዋል፡፡ ምክትል ኮማንደሩ አክለው ተከሳሹ ከነ ግብረ አበሩ ከፀጥታ መዋቅሩ እና ከህብረተሰቡ ተሸሽጎ ለማምለጥ ቢሞክርም እንዳልተሳካለትና መቼም ቢሆን ወንጀለኛ ከህብረተሰቡ እና ከፀጥታ መዋቅሩ መደበቅ እንደማይችል አውስተዋል። በፈፀሙት ወንጀልም በ06/05/2013 ዓ.ም በዋለው ችሎት 1ኛ ተከሳሽ አቶ ጌታው ሽታዬ በፈጸመው ወንጀል 12 ዓመት ከ6 ወር ጽኑ እስራት 2ኛ ተከሳሽ አቶ ሞገሽ ባቡሽ በግብረ አበርነት ተሳታፊ ሆነው በመገኘታቸው በ11 ዓመት ጽኑ እስራት መቀጣታቸውን ገልጸዋል፡፡ በመጨረሻም ምክትል ኮማንደር ወጋየሁ ቦጋለ ህብረተሰቡ ምንም አይነት ወንጀል ሲፈጸም አካባቢው ለሚገኝ የፖሊስ ኦፊሰር በመጠቆም ወንጀለኛን በጋራ መካላከል እንደሚገባ አስረድተዋል። ማንም ሰው ክህግ በታች መሆኑን በመረዳት የሴቶችና የህጻናትን መብት በማክበር እሴታችንን ባህላችንን በመጠበቅ ታሪክ አፍራሽ ትውልድ ሳይሆን ታሪክ ሰሪ ትውልድ ማፍራት ከሁሉም የማህበረሰብ ክፍል የሚጠበቅ ተግባር ነው ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ ሞረትና ጅሩ ኮሚኒኬሽን!

Source: Link to the Post

Leave a Reply