በሰሜን ሸዋ ዞን ብሬል መትረየስን ጨምሮ 153 የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች ከ17 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶች ጋር ተያዙ

በሰሜን ሸዋ ዞን ብሬል መትረየስን ጨምሮ 153 የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች ከ17 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶች ጋር ተያዙ

አዲስአ አበባ፣ ታህሳስ 28፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ብሬል መትረየስን ጨምሮ 153 የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች ከ17 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶችና ሌሎች ለወንጀል ተግባር የተዘጋጁ ቁሳቁሶች ጋር መያዙን ፖሊስ አስታወቀ።

የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የወንጀል መከላከልና የአካባቢ ሰላም ማስከበር ምክትል ዳይሬክተር ዋና ኢንስፔክተር ተሬሳ ዴሬሳ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ የጦር መሳሪያዎቹና ሌሎች ህገ ወጥ ቁሳቁሶች በቁጥጥር ሥር የዋሉት በዞኑ 13 ወረዳዎችና ሶስት የከተማ አስተዳድሮች ውስጥ ነው።

ባለፉት 20 ቀናት በተደረገ ድንገተኛ የጎዳናና የቤት ለቤት ፍተሻ ከተያዙት መሳሪያዎች መካከል ሰባት ብሬን መትረየስ፣ 19 ክላሽንኮቭ እና 127 ሽጉጦች ይገኙበታል።

እንዲሁም 17 ሺህ 451 ተተኳሽ ጥይቶች፣ አራት ቦንቦች የተለያዩ የሬዲዮ መገናኛዎችና የጦር ሜዳ መነፅሮች መገኘታቸውንም አስረድተዋል።

ከእነዚህ ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያዎችና ቁሳቁሶች ጋር ተያይዞ የተጠረጠሩ 56 ግለሰቦች ፍርድ ቤት ለማቅረብ እየተሰራ መሆኑን ዋና ኢንስፔክተር ተሬሳ ገልጸዋል።

ባለፉት ሶስት ወራት 48 ተጠርጣሪዎች ላይ በህገ ወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውር በፍርድ ቤት ተከሰው እስከ 11 ዓመት በሚደርስ እስራትና እስከ 50 ሺህ ብር እንዲቀጡ የተወሰነባቸው መሆኑንም አውስተዋል።

“ህገ-ወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውርን ለመግታት የህብረተሰቡ ተሳትፎ ወሳኝ ነው” ያሉት ዋና ኢንስፔክተሩ፤ እነዚህን መሳሪያዎች ለመያዝ ህዝቡ ድጋፍ ማድረጉን ተናግረዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post በሰሜን ሸዋ ዞን ብሬል መትረየስን ጨምሮ 153 የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች ከ17 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶች ጋር ተያዙ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply