You are currently viewing በሰሜን ሸዋ ዞን ወረጃርሶ ወረዳ ሁለት አማራዎች በአሸባሪው ኦነግ ሸኔ ታገቱ፤ ከመካከላቸው 250 ሽህ ብር እንዲከፍል የተጠየቀ መኖሩ ተገልጧል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ     ህዳር 14…

በሰሜን ሸዋ ዞን ወረጃርሶ ወረዳ ሁለት አማራዎች በአሸባሪው ኦነግ ሸኔ ታገቱ፤ ከመካከላቸው 250 ሽህ ብር እንዲከፍል የተጠየቀ መኖሩ ተገልጧል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 14…

በሰሜን ሸዋ ዞን ወረጃርሶ ወረዳ ሁለት አማራዎች በአሸባሪው ኦነግ ሸኔ ታገቱ፤ ከመካከላቸው 250 ሽህ ብር እንዲከፍል የተጠየቀ መኖሩ ተገልጧል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 14 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ወረጃርሶ ወረዳ ሞጆ ቆላ/መድፉ በተባለ አካባቢ ሁለት አማራዎች ህዳር 13/2015 በአሸባሪው ኦነግ ሸኔ ታግተዋል። የታገቱትም:_ 1) አስናቀ በሌው የ12 ዓመት ተማሪ ልጅ ሲሆን ከጠዋቱ 1 ሰዓት አካባቢ ስንቅ አዝመራ ላሉ ሰዎች አድርሶ ወደ ት/ቤት ሲመለስ የታገተ ነው እና 2) እንደሻው አሰፋ፣ እድሜው 40 ዓመት ገደማ ሲሆን ከቀኑ 10 ሰዓት አካባቢ በጤፍ ማሳው አጨዳ ላይ እያለ በሽብር ቡድኑ ታግቷል። በጸረ አማራ እና ጸረ ኢትዮጵያ አቋሙ የሚታወቀው የኦነግ ሸኔ የሽብር ቡድን በአማራ ላይ ፈርጀ ብዙ የዘር ፍጅት መፈጸሙን ቀጥሎበታል የሚሉት የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ምንጮች ከታጋቾች መካከል አንዱ 250 ሽህ ብር እንዲከፍል ተጠይቋል። በእለቱ ከቀኑ 10 ሰዓት አካባቢ ደግሞ ከ30 በላይ የአርሶ አደር ከብቶችን ዘርፈው ወስደዋል። ጥቅምት 27/2015 በጓህ ጽዮን ቀሬ ለቅሶ ለመድረስ ከሰንዳፋ የመጣች አንዲት አማራም ቱሉሚልኪ አካባቢ ከሁለት ወንዶች ጋር ታግታ በልመና ባለቤቷ 300 ሽህ ብር ከፍሎ ያስለቀቃት መሆኑ ታውቋል። ክፍያው ያለ ፍርሃትና ያለ ስጋት መሀል ከተማ ላይ እየተቀበሉ ይገኛሉ፤ 500 ሽህ ብር መሃል ከተማ ላይ ከፍሎ የተለቀቀ ሰው መኖሩ ተገልጧል። አንድ የፍልቅልቅ ሾፌርም ከአሁን ቀደም 1 ሚሊዮን ብር ተጠይቆ 700 ሽህ ብር ከፍሎ የተለቀቀ መሆኑም ተወስቷል። የኦሮሚያ ክልል መስተዳድርም ሆነ የዞንና የወረዳው መስተዳድር በንጹሃን አማራዎች ላይ የሚፈጸመው ግድያን፣ እገታን እና ዝርፊያን ለማስቆም አቅሙ ሳይሆን ፍላጎቱ የላቸውም፤ እያዩ እንዳላዩ ነው የሚያልፉት፤ብዙዎች የጥቅሙ ተጋሪዎች ናቸው ብለዋል ነዋሪዎቹ። በቱሉሚልኪ መስመር መኪና ላይ መታወቂያቸው እየታዬ የታገቱ 2 ሾፌር እና ረዳት 2 ሚሊዮን ብር ተጠይቀው ለመክፈል አቅም ባለመኖሩ ብዙ እንግልት ላይ እንደነበሩ እና ለቤተሰብ ሲባል መጨረሻቸውን በተመለከተ ግልጽ መረጃ አለመውጣቱ የሚታወስ ሲሆን፣ ሌሎች ሁለት ሾፌር እና ረዳት ደግሞ 4 ሚሊዮን ብር እንዲከፍሉ ተጠይቀው 535 ሽህ ብር ከፍለው በልመና ከግፈኞች እጅ መለቀቃቸው የሚታወቅ ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply