በሰሜን ሸዋ ዞን የሲያደብር እና ዋዩ ወረዳ መምህራን ለማበረታቻ ሽልማት ተብሎ የተመደበው በጀት አልደረሰንም በሚል ላቀረብነው ጥያቄ ምላሽ የሚሰጠን አካል አላገኘንም ሲሉ ቅሬታ አቀረቡ። አማ…

በሰሜን ሸዋ ዞን የሲያደብር እና ዋዩ ወረዳ መምህራን ለማበረታቻ ሽልማት ተብሎ የተመደበው በጀት አልደረሰንም በሚል ላቀረብነው ጥያቄ ምላሽ የሚሰጠን አካል አላገኘንም ሲሉ ቅሬታ አቀረቡ። አማ…

በሰሜን ሸዋ ዞን የሲያደብር እና ዋዩ ወረዳ መምህራን ለማበረታቻ ሽልማት ተብሎ የተመደበው በጀት አልደረሰንም በሚል ላቀረብነው ጥያቄ ምላሽ የሚሰጠን አካል አላገኘንም ሲሉ ቅሬታ አቀረቡ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 20 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በሰሜን ሸዋ ዞን ሲያደብር እና ዋዩ ወረዳ የሚገኙ መምህራን በእያመቱ ሰኔ 22 ቀን ለሚከበረው የመምህራን ቀን በሚል በመንግስት በጀት እንደሚመደብ ገልፀዋል። ባለፉት ሁለት እና ሶስት ዓመታትም መምህራንን ለማበረታት በሚል ከተመደበው በጀት ግዥ ተፈፅሞ የድርሻቸውን እንደወሰዱ አውስተዋል። ይሁን እንጅ ለ2012 ዓ.ም ሰኔ ለሚከበረው የመምህራን ቀን በሚል በጀት የተመደበ ቢሆንም በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት በዓሉ እንዳልተከበረ አውስተዋል። የሲያደብርና ዋዩ ወረዳ መምህራን እና ተወካዮች ባላወቁበት ሁኔታ በጀቱ ለልማት ውሏል መባሉ ቅሬታ ፈጥሮብናልም ብለዋል። ለመምህራን ማበረታቻ ተብሎ የተመደበ በጀቱ ያለእኛ ይሁንታ እና እውቅና ለየትኛው ልማት ዋለ በሚል ቅሬታ ብናቀርብም ከማዳፈን ያለፈ ተገቢ ምላሽ የሚሰጠን አካል አላገኘንም ብለዋል። እስካሁን ድረስ ከ10 ያላነሱ በወረዳው የሚገኙ ት/ቤቶች መምህራን ቅሬታቸውን እንዳቀረቡ የተገለፀ ሲሆን የትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጎርፉ መገርሳ ግልፅ የሆነ መረጃ ሊሰጡን አልቻሉም ብለዋል። ይህን ተከትሎም ወደ ሲያደብርና ዋዩ ወረዳ ህዝብ ቅሬታ ሰሚ ጽ/ቤት አቅንተን አቤት ብንልም የጽ/ቤት ኃላፊው አቶ ዮሀንስ ግርማ የቅሬታ ሰሚ ባለሙያውን የያዝከውን ኬዝ አቋርጥ በማለታቸው ለቅሬታችን ምላሽ ማግኘት አልቻልንም ነው ያሉት። በሲያደብርና ዋዩ ወረዳ የመምህራን ማህበር ፀሀፊ የሆኑት አቶ ደረጀ ነጋሽ መምህራን ከበጀት፣ከጂኤጅ፣ከካርታና ከእድገት ጋር በተያያዘ ያነሷቸውን ቅሬታዎች በመጋራት ለተለያዩ ተቋማት ለማቅረብ ብሞክርም እስካሁን መልስ አልተገኘም ብለዋል። የወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጎርፉ መገርሳ በኮሮና ምክንያት መምህራን ስላልነበሩና ለመወያየትም አስቸጋሪ ስለነበር በጀቱ በአስተዳደር ም/ቤቱ በኩል ተዛውሮ ለልማት ስለመዋሉ ገልፀዋል። ቅሬታው በተደራጀ መንገድ አልደረሰኝም ያሉት አቶ ጎርፉ የቅሬታ አፈታት ሂደቱን መከተል ሲገባቸው አልፈው ወደ ሚዲያ መሄዳቸው መብት ቢሆንም አላስደሰተኝም ብለዋል። በወረዳው የህዝብ ቅሬታ ሰሚ ጽ/ቤት የህግ ባለሙያ የሆኑት አቶ ሽመልስ ሀይሌ በበኩላቸው ከመምህራን የቀረበልኝን ቅሬታ መርምሬ ት/ጽ/ቤት ምላሽ እንዲሰጥበት ብጠይቅም ፈቅዶ መልስ የሚሰጥ አላገኘሁም ብለዋል። በተጨማሪም የበጀት አጠቃቀሙ እንዴት ነበር በሚል በመመሪያው መሰረት ለማጣራት ደብዳቤ ብጽፍም የጽ/ቤት ኃላፊው አቶ ዮሀንስ ግርማ ማህተም በመከልከላቸው ለመስራት አልቻልኩም ነው ያሉት። የሲያደብርና ዋዩ ወረዳ የህዝብ ቅሬታ ሰሚ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዮሀንስ ግርማም ለቀረበላቸው ቅሬታ ምላሽ ሰጥተዋል። የመምህራንን ቅሬታ እንደሚጋሩት ገልፀው ነገር ግን ከበጀት ጋር በተያያዘ ያለውን ሰነድ ለመፈተሽ የሚያስችል መመሪያ እንደሌለ ብገልጽላቸውም አንዳንዶቹ አልተረዱኝም ብለዋል። ባለሙያውንም የከለከልኩት መምሪያ ጥሶ እንዳይሰራ በሚል እንጅ የመምህራን ቅሬታ እንዳይፈታ በሚል አይደለም ሲሉ አስተባብለዋል። ቅሬታ ካቀረቡ መምህራንና ከተለያዩ የተቋማት አመራሮች ጋር ያደረግነውን ቆይታ በአሚማ የዩቱብ አድራሻ የምናጋራ ይሆናል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply