በሰሜን ሸዋ ደራ አካባቢ ሁለት አባትና ልጅ በታጣቂዎች መገደላቸው ተሰማ ። /// አሻራ ሚዲያ ጥቅምት 20/2013 ዓ.ም ባህርዳር /// የአሻራ ሚዲያ ምንጭች ከቦታው እንዳረጋገጡት የማሽላ…

በሰሜን ሸዋ ደራ አካባቢ ሁለት አባትና ልጅ በታጣቂዎች መገደላቸው ተሰማ ። /// አሻራ ሚዲያ ጥቅምት 20/2013 ዓ.ም ባህርዳር /// የአሻራ ሚዲያ ምንጭች ከቦታው እንዳረጋገጡት የማሽላ ሰብላቸውን በመሰብሰብ ላይ በነበሩ ሁለት ንጹሀን አባትና ልጅ ላይ በታጣቂ ሽፍቶች እንደተገደሉና አስክሬን ለማንሳት የአካባቢው ማህበረሰብም ሆነ የወረዳው አመራር አካላት በፍርሀትና በቸልተኝነት ተመልክተዋል ሲሉ ምንጫችን ገልጸውልናል፡፡ በደራ አካባቢ ከአሁን በፊት ብዙ ቁጥር ያላቸው ንጹሀን አማራዎች በሽፍቶች እየተገደሉ ሲሆን ከመስከረም 2013 ዓም ወዲህ ብቻ ከአስራ አምስት በላይ ንጹሀን ተገድለዋል ሲሉ ገልጸውልናል፡፡ እንደ ምንጫችን ገለጻ በአካባቢው ያለው የኦሮሚያ ልዩ ሀይል መሬቱን እንጅ ሰውን ልጠብቅ አልመጣሁም የሚል ምላሽ በተደጋጋሚ እንደሚሰጣቸው አስረድተዋል፡፡ ምንጫችን አክለውም ተደጋጋሚ የሆነውን ዘርና ብሄርን መሰረት ያደረገ ጥቃት ለማስቆም መንግስት የደራን ጉዳይ አጽኖኦት ሰጥቶ ሊመለከተው ይገባል የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ ዘጋቢ ፡-ማርሸት ጽሀው

Source: Link to the Post

Leave a Reply