በሰሜን ሸዋ ደራ አካባቢ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ጥቃት ለመፈጸም በድብቅ እየተንቀሳቀሱ መሆኑ ተሰማ !!

ደራ አካባቢ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ከሰሞኑ ጥቃት ለመፈጸም እንቅስቃሴ እያደረጉ መሆኑን የደራ ሸዋ አማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ አስሳቢ መምህር ሀይለ ሚካኤል ዓርዓያ ለአሻራ ሚዲያ በሰጡት ቃለ ምልልስ ገልጸዋል፡፡

ደራ አካባቢ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ህጻናትና ሴቶችን በማገት ከታጋች ቤተሰቦች ከ50 ሺህ ብር ጀምሮ እየጠየቁ ሲሆን ገንዘብ የለንም በማለት ምላሽ የሚሰጡ የታጋች ቤተሰቦችን ልጆች እየገደሉ እንደሆነ መምህር ሀይለ ሚካኤል ገልጸዋል፡፡

ደራ ውስጥ የወረዳውን ዋና ከተማ ደራ ጉንዶ መስቀል ጨምሮ (ከ 300 ) ሶስት መቶ በላይ የኦሮሚያ ልዩ ሀይል ቢኖርም ነዋሪዎቹ የሰላም ይከበርልን ጥያቄ ቢጠይቁም እኛ የመጣነው መሬት ለመጠበቅ እንጅ ህዝብ ለማዳን አይደለም የሚል ምላሽ ከልዩ ሀይል አባላት እንደተሠጣቸው ገልጸዋል፡፡

በመሆኑም አሁን ላይ ደራ የሚገኙ የአማራ ማህበረሰብ አባላት ከቀድሞው ሁኔታዎች ሁሉ የከፋ ችግር ውስጥ ገብተናል ሲሉ መምህር ሀይለ ሚካኤል ጨምረው ገልጸዋል፡፡

ክቡራን የአሻራ ሚዲያ ዝግት ተከታታዮቻችን ከደራ አማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ሰብሳቢ መምህር ሀይለ ሚካኤል አሰፋ ጋር የተደረገውን ሙሉ ቃለ ምልልስ ከሰዓታት በኋላ በአሻራ ሚዲያ ገብታችሁ እንድትከታተሉ እንጋብዛለን፡፡

ዘጋቢ ፡- ማርሸት ፀሐው

አሻራ ሚዲያ መስከረም 06/01/2013 ዓ.ም ባህር ዳር

Leave a Reply