በሰሜን አሜሪካ፣በአውሮፓና አውስትራሊያ የጎንደር ክፍለ ሀገር የወገራና የሰሜን አውራጃ ወረዳዎች የጠለምት አማራ ማንነት፣ወሰን፣ ሰላምና ልማት አስመላሽ የድጋፍ ኮሚቴ በሰሜን ጎንደር ዞን የአ…

በሰሜን አሜሪካ፣በአውሮፓና አውስትራሊያ የጎንደር ክፍለ ሀገር የወገራና የሰሜን አውራጃ ወረዳዎች የጠለምት አማራ ማንነት፣ወሰን፣ ሰላምና ልማት አስመላሽ የድጋፍ ኮሚቴ በሰሜን ጎንደር ዞን የአ…

በሰሜን አሜሪካ፣በአውሮፓና አውስትራሊያ የጎንደር ክፍለ ሀገር የወገራና የሰሜን አውራጃ ወረዳዎች የጠለምት አማራ ማንነት፣ወሰን፣ ሰላምና ልማት አስመላሽ የድጋፍ ኮሚቴ በሰሜን ጎንደር ዞን የአብይ ኮሚቴውን እንቅስቃሴ የሚያስተጓጉሉ አካላትን አወገዘ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መስከረም 9 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በሰሜን አሜሪካ፣በአውሮፓና አውስትራሊያ የጎንደር ክፍለ ሀገር የወገራና የሰሜን አውራጃ ወረዳዎች የጠለምት አማራ ማንነት፣ወሰን፣ ሰላምና ልማት አስመላሽ የድጋፍ ኮሚቴ በሰሜን ጎንደር ዞን የአብይ ኮሚቴውን እንቅስቃሴ የሚያስተጓጉሉ አመራሮችን አውግዟል። የድጋፍ ኮሚቴው ለአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ለአቶ ተመስገን ጥሩነህ በጻፈው ደብዳቤ በጎንደር ክፍለ ሀገር የወገራና የሰሜን አውራጃ ወረዳዎች የጠለምት አማራ ማንነት፣ወሰን፣ ሰላምና ልማት አስመላሽ ኮሚቴ በሰሜን ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ በአቶ ወርቁ ለምለሙ ላይ ያነሳውን ቅሬታ ተመልክቷል። በሰሜን ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ በአቶ ወርቁ ለምለሙ አለመተባበር ኮሚቴው ከህዝብ ጋር እንዳይገናኝ መደረጉ እንዳሳዘናቸውና ድርጊቱ ትክክል አለመሆኑንም ገልጸዋል። በጠለምትና በአዳርቃይ አማራ ላይ እየደረሰ ያለውን ሞት፣ስደትና እንግልት ተደራጅተው በውጭ ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማሳወቅ እየሰሩ መሆናቸውን የጠቀሰው የድጋፍ ኮሚቴው ህዝባችን በትህነግ የሚደርስበት በደል ሳያንሰው በዞኑ እንደ አቶ ወርቁ ለምለሙ ባሉ አንዳንድ አመራሮች የሚደርስበትን እንግልት ስንሰማ በእጅጉ አዝነናል ብሏል። በመሆኑም ከአሁን ቀደም ቅሬታው የደረሳቸው የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ጉዳዩን በውል ተመልክተው በትህነግ የተነጠቀ ማንነት እና እርስትን ለማስመለስ ለሚንቀሳቀሰው ለጎንደር ክፍለ ሀገር የወገራና የሰሜን አውራጃ ወረዳዎች የጠለምት አማራ ማንነት፣ወሰን፣ ሰላምና ልማት አስመላሽ ኮሚቴ ድጋፋቸውን እንዲሰጡ ሲል የድጋፍ ኮሚቴው በጻፈው ደብዳቤ በአማራ ህዝብ ስም ጠይቋል። የድጋፍ ኮሚቴው የአቤቱታ ደብዳቤውን ከአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር በተጨማሪ ለአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት፣ለአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽንና ለአማራ ክልል አስተዳደርና ፀጥታ ቢሮ የጻፈ መሆኑን ለአማራ ሚዲያ ማዕከል ከላከው ደብዳቤ ለመረዳት ተችሏል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply