በሰሜን ኢትዮጵያ በተፈጠሩ ግጭቶች ከ50ሺህ ሰዎች በላይ መፈናቀላቸዉን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ገለጸ፡፡

በታጠቁ ሃይሎች ምክንያት በተከሰተዉ ግጭት በአላማጣ፣ ራያ፣ ዛታ እና ኦፍላ ከተሞች ላይ የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር ከ50ሺህ በላይ መድረሱን የወረዳዉን አስተዳዳሪዎች ጠይቆ መረዳቱን አስታዉቋል፡፡

በስፍራዉ ያለዉ የሰብዓዊ ሁኔታ እጅግ ከባድ ነዉ ያለዉ ተመድ፤ በሺዎች የሚቆጠሩ ሴቶች እና ህጻናት በህይወት ለመቆየት ከፍተኛ የሆነ የሰብዓዊ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል ሲል ገልጿል፡፡

በደቡባዊ ትግራይ የምትገኘዉን የራያ አላማጣ ከተማ የፌደራሉ መንግስት ከትግራይ ክልል ሃይሎች ጋር ገብቶበት በነበረዉ ጦርነት ወቅት የአማራ ሃይሎች ተቆጣጥረዉት እንደነበር ይታወሳል፡፡

በግጭቱ ምክንያትም በደቡብ ወሎ ዞን ቆቦ 42ሺህ ሰዎች እንዲሁም በወግሀምራ ዞን ሰቆጣ ደግሞ 8ሺህ3 መቶ ሰዎች መፈናቀላቸዉን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ ዕርዳታ ማስተባበሪያ ቢሮ /ኦቻ/ አስታዉቋል፡፡

ይህን ጉዳይ በስፋት ለማጣራት ኤኤፍፒ የፌደራሉንም ሆነ የትግራይ ክልል ባለስልጣናትን ለማግኘት ተደጋጋሚ ጥረት ቢያደርግም እንዳልተሳካለት አስታዉቋል፡፡

እስከዳር ግርማ
ሚያዝያ 15 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply